ድርቅና በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮች የጤናውን ሥርዓት እየፈተኑት ነው ተባለ።
ይህንነ ያሉት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታው ዶ/ር አየለ ተሾመ ናቸው።
8ተኛው ሀገር አቀፍ የጤና አገልግሎት ኢኖቪሽንና ጥራት ጉባኤ ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
በዚሁ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት ሚኒስትር ዲኤታው ባለፉት ዓመታት የተከሰቱ እንደ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ፣ በየአካባቢው የሚከሰቱ ግጭቶች እና ድርቅ የጤና ሥርዓቱን እንደፈተኑት ነው ብለዋል፡፡
ከጤና አገልግሎት ጥራትና ደህንነት አንፃር ያሉት ችግሮች፣ ያልዳበረ የመረጃ አያያዝ እና አጠቃቀም፣ ውጤታማ ያልሆነ የሀብት አጠቃቀም፣ የአመራር መቀያየር፣ የባለሞያ ብቃት ማነስ፣ የተቀናጀ አሰራር ላይ ያለው ክፍተት፣ ያልተሟሉ የጤና መሰረተ ልማቶች፣ የግብአት አቅርቦት መቆራረጥ እና የጤና አገልግሎት ተደራሽ አለመሆን አሁን ብዙ ሊሰራባቸው የሚገቡ ችግሮች ናቸው ሲሉ አስረድተዋል፡፡
እነዚህን ችግሮች መፍታት ካልተቻለ ጤናማነት፣ ምርታማነት እና ሀገራዊ እድገትን ማረጋገጥ አይቻልም ብለዋል።
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments