ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደብላቸው የበጀት ምጣኔ የሚያስመዘግቡት ውጤት ታይቶ ብቻ እንደሚሆን ትምህርት ሚኒስቴር መናገሩ ይታወቃል፡፡
ለዚህም ከ47ቱም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የቦርድ ሰብሳቢዎችና ፕሬዚደንቶች ጋር ተነጋግሬ ከስምምነትም ደርሰናል ብሏል፡፡
ይህ አሰራር ዩኒቨርሲቲዎች ተጠያቂነት እንዲኖርባቸው፣ አሰራራቸውም እንዲፈተሽ ያደርጋልም ተብሎለታል፡፡
በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሽኔን አነጋግረናል፡፡
ሚኒስቴር ዴኤታው ዩኒቨርሲቲዎች ውጤታማነታቸው ተመዘኖ ተጠያቂ ጭምር የሚደረጉባቸው መስፈርቶች አሉን ብለውናል፡፡
በአዲሱ አሰራር እንደከዚህ ቀደሙ ተድበስብሶ የሚታለፉ ጉዳዮች አይኖርም ያሉ ሲሆን ለሚፈስባቸው ሀብትም ተመጣጣኝ ውጤት እንዲያመጡም ይጠበቃል በማለትም ያስረዳሉ፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
ማንያዘዋል ጌታሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5rs
Kommentare