የካቲት 5፣2016 - ስለተፈረመው ሰነድ ሆነ ሌሎች የኢትዮጵያን አቋም ስለሚመለከቱ ጉዳዮች ለአለም የማሳወቅ ስራ
- sheger1021fm
- Feb 13, 2024
- 1 min read
ከሶማሌላንድ ጋር ስለተፈረመው የመግባቢያ ሰነድም ሆነ ሌሎች የኢትዮጵያን አቋም ስለሚመለከቱ ጉዳዮች ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ የማሳወቅ ስራ እየሰራ መሆኑን በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የውጪ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተናገረ፡፡
የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ዶ/ር ፈቲ ማህዲ ቋሚ ኮሚቴው ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ኢትዮጵያ፣ በህዳሴ ግድቡ ላይ ስላላት አቋም፣ በሱማሌላንድና በኢትዮጵያ መካከል ስለተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ ምንነት፣ እንዲሁም ስለፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አተገባበርን በተመለከተ በ’’ፓርላሜንታዊ የዲፕሎማሲ’’ ዘርፍ እንዲያውቁ እየተደረገ መሆኑን ነግረውናል፡፡
በተጨማሪም በትግራይ ክልል ስለተከሰተው ድርቅ፣ ስለ ተሀድሶ ኮሚሽን እንዲሁም ሀገራዊ መግባባት ላይ ለመድረስ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እየሰራቸው ስላሉ ስራዎች ማብራሪያ እየሰጠ ነው ብለዋል፡፡
ቋሚ ኮሚቴው ዛሬም ከጀርመን መንግስት ከተወከሉ የፓርላማ አባላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
תגובות