ተመራጩ ባለፉት ሶስት ዓመታት የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ በሊቀ-መንበርነት መምራታቸው ተሰምቷል።
በድጋሚ የተመረጡትም የባንኩ ባለአክሲዮኖች ባካሄዱት 30ኛው መደበኛ ጉባኤ የተመረጠውና የምርጫውም ውጤት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያፀደቀለት አዲሱ የዳሸን ባንክ ቦርድ ባደረገው የመጀመሪያ ጉባኤ ላይ መሆኑን ሰምተናል።
መጪዎቹን ሶስት ዓመታት ዳሸን ባንክን በዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀ-መንበርነት እንዲያገለግሉ በድጋሚ የተመረጡት አቶ ዱላ መኮንን በአሁኑ ወቅት የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የማዕድን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ ተብሏል፡፡
![](https://static.wixstatic.com/media/b24dd6_40212b335c3b481c85c070837a0a3ca5~mv2.jpg/v1/fill/w_980,h_1306,al_c,q_85,usm_0.66_1.00_0.01,enc_auto/b24dd6_40212b335c3b481c85c070837a0a3ca5~mv2.jpg)
አዲስ የተመረጡት የቦርድ አባላት እና ባንኩን ላለፉት ሶስት ዓመታት ያገለገሉት የቦርድ አባላት የስራ ርክክብ ያደረጉ ሲሆን ንዑስ ኮሚቴዎችንም አዋቅረዋል ሲል ባንኩ ለሸገር በላከው መግለጫ ጠቅሷል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments