top of page

ታህሳስ 13፣2016 - የጋዜጠኞች እስር እና ማስፈራራት በኢትዮጵያ

  • sheger1021fm
  • Dec 23, 2023
  • 1 min read

የመገናኛ ብዙሃን ህዝብ የሚያስፈልገውን መረጃ ያለተፅዕኖ እና ያለ ማንም ጫና ማሰራጨት ካልቻሉ፣ በነፃነት መረጃዎችን ማንሸራሸር ከተሳናቸው ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት የወረቀት ላይ ጌጥ ብቻ ይሆናል፡፡


ለመሆኑ አሁን ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ በተመለከተ የመገናኛ ብዙሃን እውነታውን እና በየቀኑ የሚከሰተውን እንደልብ ለማውራት የሚፈቅድ አውድ አለ? የሚለው ብዙ የሚያነጋግር ነው፡፡


ጋዜጠኞች ባቀረቡት መረጃ ምክንያት እንደሚዋከቡና ለእስር እንደሚዳረጉም ጭምር የሲቪክ መብት ተሟጋቾች ይናገራሉ፡፡


ይህ ደግሞ ያልዳበረውን የዲሞክራሲ ባህል የሚያጠፋ በመሆኑ እንዲታረም እያያሳሰቡ ነው፡፡


 ያሬድ እንዳሻው





የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

Kommentare


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page