ሰኔ 22፣2015
የፓኪስታን የፀጥታ ኃይሎች የአገሪቱን የIS ፅንፈኛ ቡድን ከፍተኛ የጦር አዛዥን ገደልን አሉ፡፡
የፅንፈኛ ቡድኑ አዛዥ የተገደለው አገሪቱ ከአፍጋኒስታን ጋር በምትዋሰንበት የድንበር አካባቢ እንደሆነ አረብ ኒውስ ፅፏል፡፡
ሻፊ ኡላህ ከተባለው የፓኪስታን የIS ፅንፈኛ ቡድን የጦር አዛዥ ጋር ሌሎች ሁለት የቡድኑ ታጣቂዎችም መገደላቸው ታውቋል፡፡
የተገደለው የፅንፈኛው ቡድን ከፍተኛ የጦር አዛዥ በፓኪስታን መንግስት ሲፈለግ መቆየቱን ዘገባው አስታውሷል፡፡
ፓኪስታን ከአፍጋኒስታን የምትዋሰንበት የድንበር አካባቢ የተለያዩ ፅንፈኛ ቡድኖች መናኸሪያ እንደሆነ ይነገራል፡፡
የመንግስት የፀጥታ ሀይሎች ፅንፈኞቹን ለማጥፋት ተከታታይ ዘመቻ እያካሄዱ ነው፡፡
ፅንፈኞቹም አሁንም ድረስ ጥቃት እያደረሱ ነው ተብሏል፡፡
የኔነህ ከበደ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
https://bit.ly/33KMCqz
Comments