top of page

መጋቢት 6፣2016 - ዲኤምሲ የተባለ ቤት ገንቢ ኩባንያ፤ የመኖሪያ ቤቶች ገንብቶ ለፈላጊዎች ለማቅረብ ስራ መጀመሩን ተናግሯል

  • sheger1021fm
  • Mar 15, 2024
  • 1 min read

ዲኤምሲ (DMC) የተባለ ቤት ገንቢ ኩባንያ፤ እስከ ሶስት የመኝታ ክፍሎች ያላቸው የመኖሪያ ቤቶች ገንብቶ ለፈላጊዎች ለማቅረብ ስራ መጀመሩን ተናግሯል።


የኩባንያው የስራ ሃላፊዎች በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ቤቶቹ ከስድስት ሚሊዮን ብር እስከ ሃያ ሚሊዮን ብር በሆነ ክፍያ ለፈላጊዎች የሚተላለፉ ናቸው።


ቅድመ ክፍያው ከአጠቃላይ የቤቱ ዋጋ አስር በመቶ ነው የተባለ ሲሆን፤ ሙሉው ተከፍሎ የሚጠናቀቀው በዘጠኝ ዙር እንደሆነም ተነግሯል።


ቤቶቹ የአልሙኒየም ፎር ቦርድ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሚገነቡ ናቸው ያሉት የዲ ኤም ሲ ሪል ስቴት የማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ ፋንታሁን ግርማ፤ ለኑሮ ምቹ እንዲሆኑም ዲዛይን ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራቱን ተናግረዋል።


ንጋቱ ረጋሳ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page