top of page

ግንቦት  12፣2016 - ''ለመሬት መንሸራተት ተጋላጭ ናቸው በተባሉ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎችን አሰፋፈር ማስተካከል ይገባል'' ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት

ለመሬት መንሸራተት ተጋላጭ ናቸው በተባሉ የከተሞች አካባቢ የሚኖሩ ሰዎችን አሰፋፈር ከወዲሁ ማስተካከል ይገባል ሲል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳሰበ።

 

በመጪው ክረምት ይኖራል ተብሎ የሚጠበቀው ከመደበኛ በላይ ዝናብ በእነዚህ አካባቢዎች የመሬት መንሸራተት ሊያስከትል እንደሚችል ኢንስቲትዩቱ አመልክቷል።

 

በመጪው ክረምት ከመደበኛ በላይ የሆነ ዝናብ እንደሚኖር በኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ተንብይዋል።

በዚህም ክረምት ዋነኛ የዝናብ ወቅታቸው የሆኑት የሰሜን ፤ ሰሜን ምዕራብ ፤ ምዕራብ ፤ ደቡብ ምዕራብ ፤ መካከለኛው ሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የአገሪቱ አካባቢዎች ከመደበኛ በላይ የሆነ ዝናብ ያገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ፤ የኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈጠነ ተሾመ ተናግረዋል።

 

ዝናቡ ለእርሻ ስራ አመቺ ሁኔታን የሚፈጠር እንደሆነ የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሩ በግድቦችም በቂ ውሃ ለመያዝ ዕድል እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

 

 ከዚሁ ጋር ግን ጎርፍ ሊከሰት ስለ ሚችል ጥንቃቄ ይደረግ ብለዋል።

 

በከተሞችም በተለይ ለመሬት መንሸራተት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎችን አሰፋፈር ከወዲሁ ማስተካከል እንደሚገባ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል

 

ከመደበኛ በላይ የሆነው የክረምቱ ዝናብ ሲያቆም ደግሞ ወባ እና ኮሌራ በወረርሽኝ መልክ ሊከሰቱ ይችላሉ ያለው ኢንስቲትዩቱ፤ ለዚህም ከወዲሁ የቅድመ መከላከል ስራ እንዲሰራ አሳስቧል።

 

ንጋቱ ረጋሣ

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

 

 

 

Comments


bottom of page