ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከግንቦት 21 እስከ 27 በአዲስ አበባ አጀንዳ ማሰባሰብ እጀምራለሁ አለ፡፡
ኮሚሽኑ ይህን ያለው ምክክሩ እንዲሳካ ከመገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎች ጋር እያደረገ ባለው ውይይት ላይ ነው፡፡
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አምባሳደር መሐሙድ ድሪል በአዲስ አበባ ከግንቦት 21 እስከ 27 የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ይጀመራል ብለዋል፡፡
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በ10 ክልሎችና በሁለት ከተማ አስተዳደሮች በአጀንዳ አሰባሰብ ሂደት ላይ የሚሳተፉ ተወካዮችን ለይቻለሁ ብሏል፡፡
በሂደቱ ከየወረዳው 10 የማህበረሰቡ ወኪሎች ተሳትፈውበታል ተብሏል፡፡
እስካሁን በተደረገው የተሳታፊዎች ልየታ በአጠቃላይ 932 ወረዳዎች የሂደቱ አካል ሆነኗል መባሉ ሰምተናል፡፡
በተካሄደው የተወካዮች መረጣ በድምሩ 105,070 ሰዎች ተሳትፈዋል ሲል ኮሚሽኑ አስረድቷል፡፡
17210 ሰዎች ደግሞ ለአጀንዳ ማሰባሰብ ከ10ሩ ክልሎችና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች መመረጣቸው ተነግሯል፡፡
ያሬድ እንደሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments