ይህንን ያለው የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ነው፡፡
ባለስልጣኑ እንዳለው ኢትዮጵያ ውስጥ ቅርሶች አሁንም ድረስ በተለያየ መንገድ ተዘርፎ ከሀገር እየወጣ ነው፡፡
የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኤልያስ ሽኩር እንደነገሩን ጥንታዊ ቅርሶች ዛሬም ድረስ በግለሰቦች እና በሌሎች አካላት እየተሰረቁ ከሀገር ይወጣሉ፡፡
ይህም የሚታወቀው ገበያ ላይ ሲወጡ ነው፤ ከዚህ ውጪ የሚታወቅበት መንገድ የለም ያሉት አቶ ኤልያስ የቅርስ ዝርፊያውን ለመከላከል እና ቅርሶችን ለመጠበቅ ከፀጥታ አካላት ጋር በየጊዜው በጋራ እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን በተዘረፉት ቅርሶች ያህል ባይሆንም የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ዲፕሎማቶችን ተጠቅሞ ተዘርፈው ከሀገር የወጡ ቅርሶችን የማስመለስ ስራ እንደሚሰራ አቶ ኤልያስ ተናግረዋል፡፡
በዚህ አመትም የተመለሱ ቅርሶች አሉ የሚሉት ምክትል ዳይሬክተሩ ነገር ግን ቅርሶቹን ለማስመለስ ከዚህ በፊት የወጡ አለማቀፍ ኮንቬሽኖች(ስምምነቶች) የማይደግፉን ጊዜ አለ ብለዋል፡፡
ይህም ሲያስረዱ ከቅርስ ጥበቃ ጋር በተያያዘ ኮንቬሽኖች ከመፅደቃቸው በፊት የተዘረፉ ቅርሶችን ለማስመለስ በሚደረግ ጥረት ነው ህጎቹ የማይረዱን ሲሉ አስረድተዋል አስረድተውናል፡፡
የቅርስ ዝርፊያን ለማስቀረት እና ጥበቃውን አስተማማኝ ለማድረግ ከተፈለገ ማህበረሰቡ በቅርስ እድሳትና ጥበቃ ላይ እንዲሳተፍ ሊደረግ ይገባል ሲሉ ያሳስባሉ፡፡
ይህ ካልሆነ ግን ችግሩን ሙሉ ለሙሉ መከላከልእና የቅርስ ዝርፊያን ለማስቀረት አይቻልም ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቅርሶች በተለያዩ ሀገራት ተዘርፈው ብሄራዊ ሙዝየም ላይ መቀመጣቸው እና በግለሰቦች እጅ እንዳሉ ከመናገር ውጪ ምን ያህል ቅርሶች በውጪ ሀገራት ተዘርፈው እንዳለ የሚያሳይ መረጃ የለም፡፡
ነገር ግን አንዳንድ የታሪክ ፀሀፊያን እንግሊዝ ጀርመን ጣልያን እና ፈረንሳይ በርካታው የኢትዮጵያ ቅርሶች ተዘርፈው የሚገኙባቸው ሀገራት መሆናቸው ይናገራሉ፡፡
በተለይም የእንግሊዝ ጦር በአፄ ቴዎድሮስ ዘመነ መንግስት ወቅት ቁጥራቸው የበዙ ቅርሶች ዛይዘርፍ እንዳልቀረ ነው የሚታመነው፡፡
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments