ግንቦት 22፣2016 - ማዕድን አሉባቸው የሚባሉ ቦታዎች አብዛኞቹ ታጣቂዎች የሚንቀሳቀሱባቸው ናቸው ተባለ
- sheger1021fm
- May 30, 2024
- 1 min read
በኢትዮጵያ የማዕድን ሀብት አሉባቸው የሚባሉ ቦታዎች አብዛኞቹ ታጣቂዎች የሚንቀሳቀሱባቸው ናቸው ተባለ፡፡
ይህም የሀገሪቱ ማዕድን እንዳይለማ ችግር እንደሆነ ተነግሯል፡፡
የማዕድን ሀብት ባሉባችው የተለያዩ አካባቢዎች የሸመቁ ተዋጊዎችን ከቦታቸው ማስለቀቅ ከባድ ነውም ተብሏል፡፡
ከእነዚህ ቦታዎች መካከልም፤ አማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዋድላ ደላንታ፣ ኦሮሚያ ክልል ጉጂ፣ ጋምቤላ እና ቤኒሻንጉልጉሙዝ በምሳሌነት ተጠቅሰዋል፡፡
በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ የፀጥታ ችግሮች ሀገሪቱ ከማዕድን ሀብት ዘርፍ ማግኘት የሚገባትን እያሳጧት እንደሆነም የማዕድን ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኝ ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቶችን ‘’እንደ ፀጋ ተቀብሎ ከመጠቀም ይልቅ የግጭት መንስኤ’’ ሆነው እንደቆዩ አስረድተዋል፡፡
የማዕድን ሀብት ባለባቸው የአፍሪካ ሀገራት ሐብቶቹ የግጭት መነሻ እንደሆኑ በምሳሌነት ያነሱት አንድ የምክር ቤት አባል በኢትዮጵያም እየታየ ያለው ተመሳሳይ እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል ወርቅን ጨምሮ ሌሎች ማዕድን የሚመረትባቸው አካባቢ ያሉ ማህበረሰቦች ማግኘት የሚገባቸውን ጥቅም እያገኙ አይደለም ተብሏል፡፡
ማዕድን ባለባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎቸን ተጠቃሚ ለማድረግ በፈንድ መልክ፣ ለመሰረተ ልማት(ለውሃ፣ ለትምህርት ቤት፣ ለመንገድ.. ወዘተ) መገንቢያነት የሚሰጠው ገንዘብም ክልሎች ለሌላ ሲያውሉት እንደሚሰተዋልም የማዕድን ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኝ ተናግረዋል፡፡
በአሁኑ ሰዓት በክልሎች ብቻ ፈቃድ የተሰጣቸው ከ378 የማዕድን አውጪ ማህበራት በሀገሪቱ እንደሚገኙ ተነግሯል፡፡
ማንያዘዋል ጌታሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
댓글