top of page

ግንቦት 22፣2016 - ኢሰመኮ በግል ስራ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ሠራተኞች መብት ዙሪያ ከሰጠኋቸው ምክረ ሃሳቦች አብዛኞቹ አልተተገበሩም አለ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በግል ስራ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ሠራተኞች መብት ዙሪያ ከሰጠኋቸው ምክረ ሃሳቦች አብዛኞቹ አልተተገበሩም አለ።


የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የግል ስራ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ሠራተኞችን መብቶች የተመለከተ ሪፖርት፤ እና ምክር ሃሳብ መስከረም ወር ላይ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።


ኮሚሽኑ በሪፖርቱ በግል ስራ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች አማካይነት ተቀጥረው በሚሰሩ ሠራተኞች መብቶች ላይ ችግሮች እንደሚታዩ ጠቁሞ ነበር።


በተለይም ምቹ የስራ ሁኔታና ማህበራዊ ዋስትና የማግኘት፣ የመደራጀት እና ቅሬታ የማሰማት እንዲሁም በፍትህ መብቶች አተገባበር ላይ ክፍተቶች እንደሚስተዋሉ ጠቅሷል።


በእነዚህ ችግሮች ላይ የማስተካከያ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ምክረ ሃሳቦች አቅርቦ እንደነበርም፤ በኮሚሽኑ የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ስራ ክፍል ዳይሬክተር ዶክተር ብራይትማን ገብረሚካኤል አስታውሰዋል።


ይሁን እንጂ አብዛኞቹ ምክረ ሃሳቦች እየተተገበሩ አይደለም ነው ያሉት።

ሰራተኛው ከደመወዙ ቢያንስ 20 በመቶውን ማግኘት አለበት በሚለው ደንብ አፈጻጸም ላይ፤ በፍርድ ቤቶች አካባቢ ጭምር ልዩነቶች መታየታቸውን ዶክተር ብራይትማን ነግረውናል።


ኮሚሽኑ ከሰጣቸው ምክር ሃሳቦች መካከል የተፈጸሙ እና በበጎ የሚታዩ አሉ ሲሉም ዳይሬክተሩ ነግረውናል።


የኤጀንሲ ሰራተኞች ጉዳይ የሶሰትዮሽ ግንኙነት እንደሆነ የሚናገሩት ዶክተር ብራይትማን፤ ይህንኑ ልዩ ባህሪያቸውን ከግምት ያስገባ የህግ ማዕቀፍ ሊዘጋጅ ይገባል የሚል አቋም ኮሚሽኑ እንዳለውም ነግረውናል።


ንጋቱ ረጋሣ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw


Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio


Website: https://www.shegerfm.com/


Comments


bottom of page