ግንቦት 27፣2016 - የአአዩ ንግድ ስራ ት/ቤት፤ በሎጂስቲክስ መስክ የሴቶችን አስተዋፅኦ ለማሳደግ ጀርመን ከሚገኝ ዩኒቨርሲቲ ጋር ፕሮጀክት ቅርፆ እየሰራ መሆኑን ተናገረ
- sheger1021fm
- Jun 4, 2024
- 1 min read
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ንግድ ስራ ት/ቤት፤ በሎጂስቲክስ መስክ የሴቶችን አስተዋፅኦ ለማሳደግ ጀርመን ከሚገኝ ዩኒቨርሲቲ ጋር ፕሮጀክት ቅርፆ እየሰራ መሆኑን ተናገረ፡፡
የንግድ ስራ ት/ቤቱ ከፋይናንስ ዘርፍ ባሻገር ከኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ድርጅት ጋር በመተባበር በዘርፉ ያለውን የሰው ኃይል እጥረት ለመቅረፍም እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡
የትምህርት ተቋሙ ከተለያዩ የመንግስትና የግል ተቋማት ጋር በአጠቃላይ የኢንዱስትሪ ትስስር በመፍጠር የሀገሪቱን የፋይናንስ ዘርፍ ላይ ድጋፍ እያደረገ መሆኑ ተነግሯል፡፡
በሎጂስቲክስ መስክ ከኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ድርጅት ጋር በመተባበር የተቋሙን ሰዉ ኃይል ፍላጎትን ታሳቢ ያደረገ ፕሮጀክት ተግባራዊ ማድረጉን የሚናገሩት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ንግድ ስራ ት/ቤት ኃላፊው ዶ/ር ሶሎሞን ማርቆስ ናቸው፡፡
የሎጂስቲክስና ሳፕላይ ቼይን ትምህርት ክፍል በዘርፉ የሴቶችን አስተዋፅኦ ከፍ ለማድረግ ጀርመን ከሚገኘዉ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ ኦፍ በርሊን ጋር በመተባበር ፕሮጀክት ቅርፆ ወደ ተግባር መግባቱንና የዘርፉን የምርምር አቅም ለማሳደግም የፒ ኤች ዲ ፕሮግራም መጀመሩንም ዶ/ር ሶሎሞን ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ንግድ ስራ ት/ቤት በሀገሪቱን የንግድ ስራዎችን በእዉቀት ለመምራት እንዲቻል በቀጣሪዎች ፍላጎት ላይ የተመሰረቱ አዳዲስ ፕሮግራሞችን በመቅረፅ በልዩ ልዩ መስኮች በአጠቃላይ ከ 6,4ዐዐ በላይ ተማሪዎችን እያሰለጠነ መሆኑን ሰምተናል፡፡
ምህረት ስዩም
Comments