top of page

ግንቦት 28፣2016 - አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (ሰው ሰራሽ አስተውሎት)ን መጠቀም ግድ እየሆነ መጥቷል ሲሉ ባለሞያዎች ተናገሩ

አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (ሰው ሰራሽ አስተውሎት)ን መጠቀም ግድ እየሆነ መጥቷል ሲሉ ባለሞያዎች ተናገሩ፡፡


አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ስራን ለማዘመን፣ ለቅልጥፍ እና ለአዲስ ፈጠራ እና ሌሎችም ጥቅሞች አሉት የሚለው በአንድ ወገን ስራ ይነጥቃል፤ ስራ አጥ እንዲበዛ ያደርጋል የደህንነት ስጋቶች አሉበት በሚለው በሌላ በኩል ይከራከራሉ፡፡


የኢትዮጵያ መንግስትም በተደጋጋሚ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን ለመጠቀም እየሰራ መሆኑን የሚናገር ሲሆን ወጣቶች በዘርፉ እንዲሰለጥኑ ለማድረግ ሙከራ እያደረገ መሆኑን ሲናገር ይሰማል፡፡


ቴክኖሎጂው ለሀገራችን ምን ጠቀሜታ አለው ጉዳቱስ መቋቋም ይቻል ይሆን ስንል የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የሆኑትን ደረጄ እንግዳ (ዶ/ር)ን ጠይቀናቸዋል፡፡


የዩንቨርስቲው ፕሬዝዳንት እንደሚሉት አሁን #አርቴፊሻል_ኢንተለጀንስን መጠቀም አለመቻል አይቻልም ፡፡


በተለይ አሁን ላይ አለም ከኢንዱስትሪ ጀምሮ በጦርነት አውድማ ድረስ እየተጠቀመችው መሆኑና ያብራራሉ፡፡


ፕሬዝዳንቱ እንዳሉት ቴክኖሎጂው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣቱ በእጅ ስልኮቻችን ጭምር ሳናውቀው እየተጠቀምን ነው፡፡


አሁን ትኩረት አድርጎ መስራት የሚገባው፤ የሚያመጣው ጫና በተቃራኒው መቋቋም የምንችልበትን መንገድ ላይ መስራት ነው ይላሉ፡፡


የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴዕታ ባይሳ በዳዳ፤ መንግስት በአርቴፊሻል ኢንተለጀን ዙሪያ ወጣቶች እንዲበቁ ለማድረግ እየሰራ ነው ያሉ ሲሆን በተለይም ከቡራዩ ታለንት ትምህርት ቤት ጋር ስራዎች በጋራ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡


አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ 8 ዘርፎች ላይ ትኩረት ሰጥቼ እየሰራሁ ነው ያለ ሲሆን በተለይም አርቴፊሻል ኢንተለጀን፣ ኒኩለር ቴክኖሎጂ፣ ቢግ ዳታ አናሊስስ እና ሌሎችም አለም አሁን እየሰራችባቸው ያሉ የቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ምርምር እና የፈጠራ ስራ እየሰራ መሆኑን ሰምተናል፡፡


በረከት አካሉ



コメント


bottom of page