top of page

ግንቦት 28፣2016 - ‘’የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ አዋጅ’’ አተገባበር ጋር ተያይዞ በእስር የቆዩ ሰዎች ሊለቀቁ ይገባል ሲል ኢሰመኮ አሳሰበ

  • sheger1021fm
  • Jun 5, 2024
  • 1 min read

ለ10 ወራት የቆየው ‘’የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ አዋጅ’’ አተገባበር ጋር ተያይዞ በእስር የቆዩ ሰዎች ሊለቀቁ ይገባል ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አሳሰበ፡፡


በተለያዩ የክልል አካባቢዎች የተጣሉ የእንቅስቃሴ ገደቦች እንዲነሱ እና ሌሎች ማህበረሰባዊ አገልግሎቶች እንዲመለሱ ኢሰመኮ ጥሪ አቅርቧል፡፡


የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአማራ ክልል በመንግሥት እና በታጣቂ ኃይሎች (በተለምዶ “ፋኖ”) መካከል ከሚካሄደው የትጥቅ ግጭት ጋር ተያይዞ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የነበረው እና ጥር 24 ቀን 2016 ዓ.ም ለተጨማሪ 4 ወራት የተራዘመው የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ አዋጅ ተፈጻሚነት ማብቃቱን ተከትሎ በእስር የቆዩ ሰዎችን የመልቀቅ ሂደት እንዲቀጥል ኢሰመኮ ባወጣዉ አጭር መግለጫ ጠይቋል፡፡


ኢሰመኮ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈጻጸም በሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ ያለውን ተጽዕኖ በተመለከተ ክትትልና ምርመራ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን ከአዋጁ ትግበራ ጋር የተስተዋሉ ክፍተቶችንና የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን የሚያመላክቱ ሪፖረቶችን ይፋ ማድረጉን ጠቁሟል፡፡


ምክረ ሐሳቦችን ያካተተው ግንቦት 20 ቀን 2016 ዓ.ም ይፋ ያደረገውን ጋዜጣዊ መግለጫ ጨምሮ በተለያዩ ጊዜያት በርካታ የክትትልና የምርመራ ሪፖርቶች ይፋ ሲያደርግ የቆየ መሆኑ ያስተወሰዉ የኮሚሽኑ መግለጫ በዚሁ አዋጅ አተገባበር ዐውድ ውስጥ በእስር ላይ የቆዩ ሰዎች እንዲለቀቁ ጥይቋል፡፡


ወደ መደበኛው የሕግ አተገባበር ሂደት መመለስ እንዲሁም በተለያዩ የክልል አካባቢዎች የተጣሉ የእንቅስቃሴ ገደቦች እንዲነሱ እና ሌሎች ማህበረሰባዊ አገልግሎቶች እንዲመለሱ ኢሰመኮ በመግለጫዉ ጠይቋል፡፡

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page