top of page

ግንቦት 3፣2016 - መንግስት የሚያስራቸው ጋዜጠኞች እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች

#ግጭት፣ እገታ፣ ግድያና መሰል የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ የሚከሰቱ አሰቃቂ ድርጊቶች ቢሆኑም በመገናኛ ብዙሃን ዜና ሆነው ሲዘገቡ እምብዛም አንሰማም፡፡


ጋዜጠኞች ለራሳቸውም የደህንነት ስጋት አለባቸው የሚሉ ብዙዎች ናቸው፡፡


ይህም የተጠቀሱትን መሳይ ሁነቶችን ከመዘገብ እንዲቆጠቡ አድርጓቸዋል እየተባለ ነው፡፡


ጋዜጠኛነት የሙያ ነፃናት ካጣ ደግሞ የአንድ ሃገር የዲሞክራሲ ጉዞም መቀጨጩ የማይቀር ነው፡፡


ታዲያ በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ምን እየሰራ ነው?


#የሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ መሞገት፣ የመንግስትን ብልሹ አሰራር በማጋለጥና ከተሳሳተ አካሄዱ እንዲመለስ መስራት መሰረታዊ የጋዜጠኛነት ሙያ ያስገድዳል፡፡


በሌላ በኩል ግን የጋዜጠኞች የሙያ ነፃነት በማይከበርበት ሃገር የጋዜጠኝነትን መርህ ተከትሎ መስራት ቀላል አይሆንም፡፡


አሁን በኢትዮጵያ የሚታየው ፖለቲካዊ ችግር ደግሞ የጋዜጠኝነትን ሙያ በእጅጉ እየፈተነው እና ገለልተኛ ጋዜጠኝነት እንዳይኖር ጫና መኖሩ ነው ይላሉ የዘርፉ ባለሙያዎች፡፡


መፍትሄው ምን ይሆን?


#ተቃውሞና ተፅዕኖ ተለይቶት የማያውቀው የኢትዮጵያ ፖለቲካ እንደ ጋዜጠኞች ሁሉ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾን ስራም ያከበደ ሆኖ መቀጠሉ ይነገራል፡፡


የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከልም በአሁኑ ጊዜ 10 የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እስር ላይ መሆናቸውን ይናገራል፡፡


ስለጉዳዩ ጠይቀናል::


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw


Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio


Website: https://www.shegerfm.com/


Comments


bottom of page