የውጭ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ዘርፍ ሊሳተፉ ሲመጡ የራሳቸውን ሃብት ይዘው እንዲመጡ ቢጠበቅም ከባንኮች የመበደር አዝማሚያ ያሳያሉ ተባለ፡፡
ባጠቃላይ ባለፉት 31 ዓመታት ቀጥታ ኢንቨስትመንት ተሳትፎ የቁጥርም የጥራትም ችግር ያለበት መሆኑን የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ያካሄደው ጥናት አሳይቷል፡፡
ጥናቱ በዋናነት ትኩረት ያደረገው የውጪ ቀጥታ ኢንቨስትመን ላይ ነው፡፡
በዚህም ላለፉት 31 ዓመታት ለኢትዮጵያ ያመጣወን ለውጥ ምን ድነው? ሚናውስ?
ተሳትፎውስ ምን ይመስላል ምን አይነት ችግሮች በዚህ ቀጥታ ኢንቨዝትመንት ገጥሞታል የሚለውን ዳሷል፡፡
ጥናቱ ይህንን ከተመለከተ በኋላ ለነዚህ ክፍተቶች እንደመፍትሄ ያላቸውን አስቀምጧል፡፡
ታዲያ በኢትዮጵያ ባለፉት 31 አመታት ውስጥ 6136 የውጭ ባለሀብቶች ፍቃድ የወሰዱ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 58 ከመቶ የሚሆኑት ብቻ ወደ ስራ መግባታቸው ሰምተናል፡፡
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6I
Commentaires