top of page

ግንቦት  8፣2016 - ባለፉት 10 ወራት 11.8 ቢሊዮን ብር  የተገመቱ የኮንትሮባንድ እቃዎች  መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር ተናገረ

ባለፉት 10 ወራት ከገቢ ግብር  ከ425 ቢሊዮን ብር በላይ  መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር ተናገረ።

 

ሚኒስቴሩ የ10 ወራቱን አፈፂፀም አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ ነው ይህንን ያለው።

 

ዓመቱን  ሲጀምር ለመሰብሰብ ያቀደው 442.8 ቢሊዮን ብር መሆኑንና ከዚህም ከ425 ቢሊዮን ብር በላዩን መሰብሰቡን ተናግሯል፡፡

 

ይህም የእቅዱን 96 በመቶ መሆኑን የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ ተናግረዋል።

 

ከገቢው ውስጥ በአብዛኛው ማለትም ከ 271 ቢሊዮን በላዩ ከሃገር ውስጥ ሲሰበሰብ ቀሪው ከ153 ቢሊዮን በላዩ ደግሞ ከወጪ ንግድ ቀረጥና ታክስ የተሰበሰበ መሆኑን ሸገር ሰምቷል።

 

አሰባሰቡም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ 54.7 ቢሊዮን ብር ጭማሪ ማሳየቱን ሚኒስትሯ ጠቁመዋል።

በኮንትሮባንድ በኩልም ግምታዊ ዋጋቸው 11.8 ቢሊዮን ብር የሆነ  የወጪ እና ገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች  ባለፉት 10 ወራት መያዛቸውን ሚኒስትሯ ወ/ሮ አይናለም በሰጡት መግለጫ ጠቅሰዋል።

 

ከተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል 8 ቢሊዮን ብር የሚያወጠቱ የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎቹ ሲሆኑ 3.8 ቢሊዮን ብር የሚያወጡት ደግሞ የወጪ  ኮንትሮባንድ እቃዎች ናቸው ተብሏል።

 

ከእቃዎቹ በተጨማሪ መጠኑን በቁጥር ያልገለፁት ህገወጥ ገንዘብ መያዙንም ሚኒስትሯ ሲናገሩ ሰምቷል።

 

ምንታምር ፀጋው

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

 

 

 

Comentarios


bottom of page