ዛሬም ድረስ በኢትዮጵያ ወደ 500 ወረዳዎች የነዳጅ ማደያ የላቸውም ተባለ፡፡
ይህን ያለው የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ነው፡፡
የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የነዳጅ ውጤቶች ግብይትን ሥርዓት ለመደንገግ የተዘጋጀው #አዋጅ ላይ ለማፅደቅ በጠራው መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው ይህን የተናገሩት፡፡
ዳይሬክተሯ ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት እና እኛ ካለን የህዝብ ብዛት መጠን ያለን የነዳጅ ማደያ ዝቅተኛ ነው ብለዋል፡፡
#የነዳጅ_ማደያ ግንባታ እየተካሄደ ያለው ጠረፍና ምንም የኢኮኖሚ ፋይዳ በሌለባቸው አካባቢዎች መሆኑ ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡
የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በዛሬው እለት የነዳጅ ውጤቶችን ግብይት ሥርዓት ለመደንገግ የተዘጋጀውን አዋጅ የሰላ ትችት ቢቀርብበትም በአበላጫ ድምጽ አጽድቆታል፡፡
አዋጁ በነዳጅ ግብይት ላይ የሚታየውን ‘’መሰረታዊ ችግር ከመፍታት ይልቅ ቅጣት ላይ ያተኮረ ነው’’ የሚል ትችት ቀርቦበታል፡፡
አዋጁ የተጋነነ ቅጣት በውስጡ የደነገገ መሆኑን የተናገሩት የምክር ቤት አባል ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ‘’ይህም በለሀብቱን እዳያሸማቅቅ ስጋት አለኝ ለምን አዋጁ ቅጣት ላይ ከማተኮር መሰረታዊ ችግሩን መፋታት ላይ አለተኮረም?’’ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
ከሀገሪቱ ወንጀል ህጎች ጋር እንዳይጣረስ አዋጁ ታይቷል ወይ የሚልም ጥያቄም ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) አክለዋል፡፡
የባለስልጣኑ ዳይሬክተር ሳሃረላ አበዱላሂ በሰጡት ምላሽ ቅጣቱ የተጋነነ አንዳልሆነ ተናግረው በረቂቁ ላይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካት ጋርም ተነጋግረናል ብለዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድመጡ…
ያሬድ እንዳሻው
Comments