አሜሪካ እና አጋሮቿ ለዩክሬይን ተጨማሪ የጦር መሳሪያ እርዳታቸውን ሊያጎርፉላት ነው ተባለ፡፡
አሜሪካ ብቻ 2.5 ቢሊዮን ዶላር የዋጋ ግምት ያላቸው ብረት ለበስ የጦር ተሽከርካሪዎችን እና የአየር መከላከያዎችን ለዩክሬይን ለማቅረብ መሰናዳቷን ዴፌንስ ብሎግ ፅፏል፡፡
ከአሜሪካ በተጨማሪ ብሪታንያ፣ ፖላንድ፣ ላቲቪያ፣ ኔዘርላንድስ፣ ስሎቫኪያ ለዩክሬይን የጦር መሳሪያዎችን እንልካለን ካሉ አገሮች ከብዙ በጥቂቱ ናቸው ተብሏል፡፡
አገሮቹ ለዩክሬይን ተጨማሪ የጦር መሳሪያ እና የወታደራዊ ቁሳቁሶችን ለማቅረብ ቃል ቢገቡላትም ኪየቭ ያስፈልጉኛል ያለቻቸው ከባባድ ዘመን አፈራሽ ታንኮች ግን ከጦር እርዳታው ዝርዝር ውስጥ እንደሌሉ ታውቋል፡፡
ፖላንድ እና ፊላንድ ለዩክሬይን ጀርመን ስርቶቹን ሊዮፓርድ ታንኮችን እንሰጣለን ቢሉም የበርሊን ይሁንታ እንደሚያሻቸው ተጠቅሷል፡፡
አሜሪካ እና አጋሮቿ ለዩክሬይን በሚቀርበው የጦር መሳሪያ እርዳታ ጉዳይ ዛሬ በጀርመን ተሰብስበው እንደሚመክሩ ተሰምቷል፡፡
የኔነህ ከበደ
ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Comments