የሴራሊዮን ፓርላማ የሴቶችን መብት ፣ ኑሮ እና የሥራ ሁኔታ የሚያሻሽል ሕግ አፀደቀ፡፡
ሕጉ 30 በመቶዎቹ የስራ ቦታዎች በሴቶች እንዲያዙ የሚጠይቅ መሆኑን ብሉምበርግ ፅፏል፡፡
የስራ ቦታዎች ድልድሉ የግል ድርጅቶችንም እንደሚጨምር ታውቋል፡፡
ሴቶች በስራ ቦታዎች የእኩል መብት እና ስልጠናዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል ሕግ መሆኑ ተነግሮለታል፡፡
ከ25 ያላነሱ ሰዎች ቀጥረው በሚያሰሩ ድርጅቶችም ህጉ ተፈፃሚ እንደሚሆን ታውቋል፡፡
የሴራሊዮን መንግስት ህጉ የፀደቀበትን እለት ታሪካዊ ሲል ማሞካሸቱን ዘገባው አስታውሷል፡፡
የኔነህ ከበደ
ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Comments