‘’የራያ አላማጣ ዞን በመንግስት በኩል ተዘንግቷል’’ ሲሉ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የተሰየሙት አስተዳዳሪ ተናገሩ፡፡
አካባቢው በ #ኮማንድ_ፖስት እየተዳደረ ቀጥሏል ተብሏል፡፡
በራያ አላማጣ፣ ኮረም፣ ወፍላ፣ ዛታና የተለያዩ ወረዳዎች ዛሬም የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዝግ እንደሆኑ ነው፡፡
የትምህርት የጤናና ሌሎች መሰረታዊ የሚባሉ ነገሮች በአብዛኛው እየተሰጡ እንዳልሆነ ሰምተናል።
የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ያቆሙት ከ #ፕሪቶሪያው_የሰላም ስምምነት በኋላ መሆኑን ዞኑ ለሸገር ሬዲዮ ተናግሯል፡፡
ከዚህ ቀደም #በመንግስት_ስራ ላይ የነበሩ ሰራተኞች እጃቸውን አጣጥፈው ከተቀመጡ ሰንበትበት ማለታቸውንም ነግረውናል፡፡
ከአንድ ዓመት በላይ ዝግ የሆኑት እነዚያ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወደ ስራ የሚገቡት መቼ ነው የሚለው የማህበረሰቡ ጥያቄ ሆኖ ቀጥሏል፡፡
ዞኑ ከፌዴራል ወይም ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲሁም ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ቀደም ብሎ ስፍራውን ሲያስተዳደር በነበረው የአማራ ክልል በኩል ቋሚ በጀት አልተያዘለትም ተብሏል፡፡
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5rs
コメント