የአዕምሮ እድገት ውስንነት እና የአካል ጉዳት ያለባቸው ልጆቻችንን ይዘን ወደ መንግስትም ሆነ የግል ትምህርት ቤቶች ስንሄድ፤ ትምህርት ቤቶቹ እንቀበልም ይሉናል በማለት ወላጆች በተደጋጋሚ ሲናገሩ ይሰማሉ፡፡
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በበኩሉ፤ በኢትዮጵያ ካሉ አካል ጉዳተኛ ህፃናት ከ85 እስከ 90 በመቶዎቹ የትምህርት እድል አያገኙም ሲል ባሳለፍነው ታህሳስ ወር ላይ ተናግሮ ነበር፡፡
የአዲስ አባባ አካል ጉዳተኞች ማህበርም ት/ት ቤቶች ልጆቹን አንቀበልም በማለታቸው ወላጆች እየተማረሩ ናቸው ብሎናል፡፡ የማህበሩ ፕሬዚደንት ወይንሸት ግርማ (ዶ/ር) እነዚህ ወላጆች ተሰብስበው ክስ ቢመሰርቱ ተቀባይነት አላቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ታዳጊ ሀያት ከድር፤ ‘’አንድንት የአዲስ አባባ አካል ጉዳተኛ ህጻናት ማህበር’’ ሰብሳቢ ናት፡፡ አካ ጉዳተኛ ህጻናትና ታዳጊዎች የበዙ ችግሮች እንደሚገጥሟቸው ታነሳለች፡፡ ትምህርት ቤት የገቡትም ቢሆን የመማሪያ ቁሳቁሶች ስለማይሟሉላቸው በተገቢው ትምህርቱን ይማራሉ ማለት እንደማይቻልም ትናገራለች፡፡
በተጨማሪም በርካታ ወላጆች የአካል ጉዳት እና የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ልጆቻቸውን በግንዛቤ ችግር የተነሳ እንኳንስ ትምህርት ቤት ሊወስዷቸው ይቅርና ከቤት አያስወጧቸውም ብላናልች፡፡
በአካል ጉዳተኛ ህፃናት እና ሴቶች ዙሪያ የሚሰራው ‘’የራስ አገዝ ቡድን አሠራር፣ ድርጅቶች ኅብረት (ኮሳፕ)’’ ድርጅት ስራ አስኪያጅ፤ ዮሴፍ አካሉ አሁን በረቂቅ ደረጃ ያለውና አካል ጉዳተኞችን የተመለከተው አዋጅ የአካል ጉዳተኞችን መብት የሚጥሱትን ተጠያቂ የሚያደርግ መሆን አለበት ብለውናል፡፡
ይህንን ጉዳይ በተመለከተ፤ ጉዳዩ ከሚመመለከታቸው ተቋማት መካካል አንዱ የሆነው የአዲስ አበባ ሴቶች፣ ህጻናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮን በጠይቀናል፡፡ በቢሮው የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋዊያን ግንዛቤ ስርጸት እና ንቅናቄ ብድን መሪ አየሁ ደመቀ፤ ትምህርት ቤቶች እነዚህን ልጆች እንቀበልም እንደሚሉ መረጃዎች ይደርሱናል እኛም እናውቃለን ብለውናል፡፡
ይህ የሆነውም ተጠያቂነት ስላለሰፈነ እንደሆንም ጠቅሰዋል፡፡ ችግሩ ለአንድ አካል የሚተው ጉዳይ ሳይሆን ሁሉም በያገባኛል ሊሰራበት የሚገባ ነውም ይላሉ ሀላፊዋ፡፡ አሁን እነዚህን ልጆች አንቀበልም የሚሉ አካላት ነገ ከነገ ወዲያ የእነሱ ልጆች መሰል ችግር እንደማያጋጥማቸው ምን ዋስትና አላቸው ሲሉም ይጠይቃሉ፡፡
ከላይ ለተነሳው ችግር በመንግስት እንደ መፍትሄ እየተሰራበት ያለው የአካቶ ትምህርትን ነው፡፡ ይህ የአካቶ ትምህርት ተግባራዊነቱ ምን ያህል ነው ያልናቸው ወ/ሮ አየሁ ለውጦች አሉ ግን በሚፈለገው ደረጃ ግን አይደለም ሲሉም መልሰዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)፤ ህጻናቱን ለምድነው እንቀበልም የምትሉት ብዬ ትህርት ቤቶቹን ስጠይቃቸው፤ የመማሪያ ቦታ፣ የመምህር ባጠቃላይ የአቅም ችግር ስላለብን ነው ብለውኛል ማለቱም የታወሳል፡፡
ነገር ግን ትምህርት ቤቶቹ የያቀረቡልኝ ምክንያት አላሳመነኝም፤ ብሎ ነበር በወቅቱ ኢሰመኮ፡፡
ማንያዘዋል ጌታሁን
Comments