በበጀት ዓመቱ 6 ወራት በአዲስ አበባ ከተማ የልደት ምዝገባ ከፍተኛ ቁጥር አስመዝግቧል ተባለ።
በስድስት ወራት ውስጥ በከተማው ከተወለዱ ህፃናት ውስጥ 37,750 ለመመዝገብ አቅጄ 41,183 መመዝገብ ችያለው ሲል የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ተናግሯል።
ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር ብልጫ አሳይቷል ተብሏል።
እነዚህ የጋብቻ፣ የልደት፣ የፍቺ፣ የሞት እንዲሁም የጉዲፈቻ ምዝገባዎች በወቅቱ በዘገየ የጊዜ ገደቡ ያለፈበት ተብሎ እንደሚመዘገብ ሰምተናል።
በ6 ወራት ውስጥ ጋብቻ ከ7,000 በላይ ለመመዝገብ ታቅዶ 4,935 ተመዝግቧል የተባለ ሲሆን ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር በ4.5 በመቶ መቀነሱ ተነግሯል፡፡
ፍቺን በተመለከተ 4,873 ለመመዝገብ ታቅዶ 3,769 ፍቺ መመዝገብን ተመልክተናል ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር ብልጫ አሳይቷል ተብሏል፡፡
ሞት በወቅቱ ከ5,600 በላይ ለመመዝገብ ታቅዶ 2,917 እንደተመዘገበ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ተናግረዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…
ማርታ በቀለ
Comments