የማስታወቂያ ኢንዱስትሪውን የበለጠ የሚያዘምን የ3D ማስታወቂያ ስክሪን አዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ወደስራ ሊያስገባ መሆኑን ‘’አፔክስ ትሬዲንግ’’ ተናገረ፡፡
ወደ ስራ የሚገባው ቴክኖሎጂ የኤልሲዲ እስክሪን የማስታወቂያ ዘርፍን የበለጠ ያዘምነዋል ተብሏል፡፡
አዲስ አበባ ውስጥ አሁን ላይ የኤልሲዲ ስክሪን በተለያዩ አካባቢዎች እየተስፋፋ መሆኑን የአፔክስ ትሬዲንግ ስራ እስኪያጅ የሆኑት አቶ ሮቤል ደጉ ይናገራሉ፡፡
አሁን እነሱ እያስተዋወቁት ያለው የ3D ቴክኖሎጂ ባደጉት ሃገራት ስራ ላይ ውሏል ተብሏል፡፡
በኢትዮጵያ ስራ ሲጀምርም በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያው ይሆናል ብሏል ተቋሙ፡፡
አዲሱ ኤልዲ እስክሪን ቴክኖሎጂ ምሽት አካባቢ በሌሎች እስክሪኖች ላይ የሚነሳውን የብርሃን ጨረር ችግር የቀረፈ ነው ተብሏል፡፡
ቴክኖሎጂው ራሱ መቆጣጠር ከሁኔታዎች ጋር መናበብ ስለሚችል ከብርሃን ጋር የሚነሳውን ቅሬታም የሚፈታ ነው ሲሉ አቶ ሮቤል ተናግረዋል፡፡
ይህ ቴክኖሎጂ ወደ ሀገር ቤት ለማምጣት ያስፈለገው የማስታወቂያ ዘርፉን ለማሳደግና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ሃገር ቤት ለማስገባት በማሰብ መሆኑን የአፔክስ ስራ አስኪያጅ አቶ ሮቤል አስረድተዋል፡፡
የ3D ቴክኖሎጂን ይዟል የተባለው አዲሱ የኤልሲዲ የማስታወቂያ እስክሪን አዲስ አበባ መንገዶች አካባቢ ሚታየውን የማስታወቂያ ወጥ ያለመሆን ችግር ይቀርፏል የሚል እምነት አለኝ ሲል ድርጅቱ ተናግሯል፡፡
በረከት አካሉ
Comments