ባንኮች ለአምራች ኢንዱስትሪው ፋይናንስ ከማቅረብ ይልቅ በተለመደው መንገድ የአጭር ጊዜ ትርፍ ወደ ሚያስገኝና ስጋታቸው ዝቅተኛ በሆኑ ዘርፎች ላይ ተሰማርተው እንዳይቀጥሉ አሰራሩን መፈተሸ ያስፈለጋል ሲሉ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ ተናገሩ፡፡
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ይህን ያሉት የመ/ቤታቸውን የ6 ክንውን ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት ነው፡፡
ባንኮች ስጋታቸው ዝቅተኛ እና የአጭር ጊዜ ትርፍ ወደሚያስገኙ ዘርፎች ላይ ተሰማርተው እንዳይቀሩ ማድረግ የሚልበትን አሰራር ማየት ይገባናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም ለአምራች ዘርፉ ሲቀርብ የነበረው ከ13 በመቶ ያልበለጠው የብድር አቅርቦት ድርሻ ወደ 24 በመቶ እንዲያድግ የፖሊሲ አቅጣጫ ቢሰጥም እስካሁን የደረሰው ግን 16 በመቶ ነው ብለዋል፡፡
ለአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች የስራ ማስኬጃ ብድር ባንኮች ካላቸው ካፒታል ከአንድ በመቶ ያልበለጠው ወደ 10.3 ከፍ እንዲል መደረጉን ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡
ለአምራች ዘርፉ ለግብዓት አገልግሎት ባለፉት 6 ወራት 468 ሚሊዮን ዶላር በላይ ብድር ለማቅረብ ታቅዶ ከ369 ሚሊዮን ዶላር በላይ ቀርቧል ብሏል፡፡
እቅዱን ማሳካት ያልተቻለው ደግሞ የውጪ ምንዛሬ ለማግኘት ባንኮች የሚጠይቁት የማስያዥያ ብር ከወትሮ ከፍ በማለቱ ነው ሲሉ አቶ መላኩ አለበል አስረድተዋል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
Comments