የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የቡርኪናፋሶ መንግስት የፈረንሳይ ወታደሮች ይውጡልኝ ማለቱን በጭራሽ አልገባንም አሉ፡፡
ኢማኑኤል ማክሮን ከቡርኪናፋሶ መንግስት ተጨማሪ ማብራሪያ ያሻናል ማለታቸውን ፍራንስ 24 ፅፏል፡፡
እንደሚባለው ፈረንሳይ በቡርኪናፋሶ 400 ወታደሮች አሏት፡፡
የቡርኪናፋሶ መንግስት የፈረንሳይ ወታደሮች ከአገሩ ለቅቀው እንዲወጡ መወሰኑን ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ግርታ እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል፡፡
በዚህም ምክንያት ማብራሪያ ያሻናል ማለታቸው ተሰምቷል፡፡
ይሁንና የቡርኪናፋሶ ወታደራዊ መንግስት ማክሮን የሚሹትን ማብራሪያ ለመስጠት ስለመሰናዳቱ የታወቀ ነገር የለም ተብሏል፡፡
የኔነህ ከበደ
ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Comments