top of page

ጥር 16፣2016 - ሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ 2 አልበሞችን በአንድ ቀን ሊለቅ ነው።

ከ2 ሳምንት በኋላ የሚለቁቀት የሮፉናን የሙዚቃ አልበሞች "ሐራንቤ" እና "ኖር" የሚል መጠሪያ መያዛቸውን  ሙዚቀኛው በዛሬው እለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግሯል።


ሐራምቤ በህብረት ውስጥ ያለ የራስ ቀለምን አጉልቶ ማሳየት ላይ ትኩረት ሀሳብ እንዳለው ያስረዳው ሙዚቀኛው ኖር የሚለው አልበም ደግሞ ለአዲስ ሀሳብ፣ ለአዲስ ህይወት፣ ለአዲስ ፍልስፍና እና ለአዲስ ነገር መሻትን የሚያሳይ ነው ብሏል።


በሙዚቃ ዝግጅቱ ላይ ብርቱ ጥረት እናዳደረገበት የተናገረው ሙዚቀኛው ለሁለቱ አልበሞች "ዘጠኝ" የሚል የጋራ መጠሪያ እንደሰጣቸው አስረድቷል።



ይህም ከዚህ በፊት የሰራቸው የሦስት እና የስድስት ልበሞች  መደምደሚያ መሆኑን ሰምተናል።


ሁለቱ አልበሞች በአጠቃላይ 21 ሙዚቃዎችን ይዘዋል ተብሏል።


የአብዛኛው ሙዚቃዎች ድርሰትም ሆነ ቅንብር የራሱ መሆናቸውን ያስረዳው ሮፍናን ኑሪ፤ ሃይሌ ሩት፣ሸዊት መዝገቡ፣ የልጅ ተመስገን ልጆች፣ ሶል ሮሚዮ እንዲሁም ከአለም ዓቀፉ የሬጌ ሙዚቀኛ ክሮኒክስ ጋር በጥምረት የሰራቸው ሙዚቃዎች በአልበሞቹ ውስጥ መካተታቸውን ሰምተናል።


አልበሞቹ በሮፍናን "ዩቲዩብ" ቻናልና፣ስፖቲፋይ ጨምሮ በሌሎች የዲጂታል ሙዚቃ ማቅረቢያ መንገዶች ፱በኩል ይለቀቃሉ ተብሏል።


ከአልበሙ ውስጥ ለሁለቱ ሙዚቃ ቪዲዮዎች ተሰርተዋልም ተብሏል።

ንጋቱ ሙሉ


Comentários


bottom of page