ጥር 16፣2016 - የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጉዞ ትኬቶችን በሳፋሪኮም ኤም-ፔሳ በኩል መግዛት የሚያስችል ሰምምነት ተፈረመ
- sheger1021fm
- Jan 25, 2024
- 1 min read
በሳፋሪኮም ኤም-ፔሳ በኩል የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጉዞ ትኬቶችን መግዛት የሚያስችል ሰምምነት ተፈረመ፡፡
ስምምነቱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የንግድ ዘርፍ ዋና ሀላፊ አቶ ለማ ያዴቻ እና የሳፋሪኮም ኤም-ፔሳ የዲጂታል ፋይናንስ ዋና ሃላፊ ፖውል ካቫቩ ተፈራርመውታል፡፡
በስምምነቱ መሰረት የሳፋሪኮም ኤም-ፔሳ ደንበኞች የጉዞ ትኬቶቻቸውን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሞባይል መተግበሪያ፣ ድረ-ገጽ ወይም በአየር መንገዱ አለም አቀፍ የጥሪ ማእከል በኩል እንዲገዙ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡
ይህም ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ቀልጣፋ እና አስተማማኝ ክፍያዎችን ለመፈጸም ያስችላል ተብሎለታል።
የሳፋሪኮም ኤም-ፒኤሳ ደንበኞች ከዚህ በኋላ የኢትዮጵያ አየር የጉዞ ትኬቶችን ፣ የበረራ ለይ ግዢዎችን፣ የሻንጣ ክፍያ እና ሌሎች ከፍያዎችን በቀላሉ ማከናወን ይችላሉ ተብሏል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments