top of page

ጥር 2፣2016 - የባህር ማዶ ወሬዎች

  • sheger1021fm
  • Jan 11, 2024
  • 1 min read

#ደቡብ አፍሪካ


ደቡብ አፍሪካ በአለም አቀፍ ፍርድ ቤት በእስራኤል ላይ በዘር መጥፋት ወንጀል በከፈትኩት ክስ የሌሎች ሀገሮች እርዳታ አያሻኝም አለች፡፡


ደቡብ አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ፍርድ ቤት በእስራኤል ላይ የክስ ፋይል የከፈተችው እስራኤል በጋዛ የጦር ዘመቻዋ በፍልስጤማውያን ሰላማዊ ሰዎች ላይ የዘር ፍጅት እየፈፀመች ነው ብላ እንደሆነ ሚድል ኢስት ሞኒተር ፅፏል፡፡


የተወሰኑ ሀገሮችም ደቡብ አፍሪካን አይዞሽ ከጎንሽ ነን እንረዳሻለን እያሏት ነው፡፡


የደቡብ አፍሪካ መንግስት እርዳታችሁ አያሻኝም ጉዳዩን ለብቻዬ ዳር የማድረስ አቅሙ አለኝ ማለቱ ተሰምቷል፡፡


የደቡብ አፍሪካ መንግስት ሌሎች አገሮች ተጨማሪ ማስረጃ እናቀርባለን ማለታቸው አሁን የተጀመረውን ሂደት ሊያጋትተው ይችላል የሚል ስጋት አለው ተብሏል፡፡




የየመን ሁቲዎች በቀይ ባህር ተላላፊ መርከቦች ላይ የሚፈፅሙትን ጥቃት እንዲያቆሙ በፀጥታው ምክር ቤት ተጠየቁ፡፡


ምክር ቤቱ ሁቲዎቹ ቀደም ሲል የያዟትን ጋላክሲ ሊደር የተሰኘች መርከብ እንዲለቁም መጠየቁን ኒውስ 18 ፅፏል፡፡


ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት ያላቸው የምክር ቤቱ ቋሚ አባላት ሩሲያ እና ቻይና ግን ድምፀ ተአቅቦ ማድረጋቸው ታውቋል፡፡


ቢቢሲ እንደፃፈው ደግሞ አሜሪካ እና ብሪታንያ ከምክር ቤቱ ውሳኔ አስቀድሞ በሁቲዎቹ ላይ የጦር እርምጃ እንደሚወስዱ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡


ከሁቲዎቹ ተተኩሰዋል ያሏቸውን 21 አጥቂ ሰው አልባ በራሪ አካላት /ድሮኖች/ እና ሚሳየሎችን ማምከናቸውን የጦር ሹሞቻቸው ተናግረዋል፡፡


ድሮኖቹ እና ሚሳየሎቹ ያደረሱት አንዳችም ጉዳት የለም ብለዋል፡፡


በቀይ ባህርም ጦርነቱ መጣሁ መጣሁ እያለ ነው፡፡



በስዊድን የመከላከያ ሹሞች የሰጡት የጦር ዝግጁነት ማስጠንቀቂያ ዜጎቹን በምንድነው ነገሩ በእጅጉ እያሳሰበ ነው ተባለ፡፡


የሲቪል እና ወታደራዊ የመከላከያ ሹሞች በየፊናቸው የሀገሩ ሰዎች ለጦር ወቅት እንዲዘጋጁ የማስጠንቀቂያ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ቢቢሲ ፅፏል፡፡


ያም ሆኖ ሹሞቹ የጠቀሱት ተጨባጭ የጦርነት ምልክት የለም ተብሏል፡፡


ዜጎች ደግሞ በድረሱልን ጥሪ ማሰሚያ የስልክ መልዕክት በምንድነው ነገሩ ጥያቄ ማብዛታቸው ተሰምቷል፡፡

የመከላከያ ሹሞች ግን ለማንኛውም በአዕምሮ ዝግጁ ሆኖ መጠበቁ ይሻላል ብለን ያስተላለፍነው መልዕክት ነው ብለዋል፡፡


ስዊድን ጥያቄዋ በቱርክ እና በሐንጋሪ የሚደገፍላት ከሆነ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት(NATO) አባል መሆኗ እንደማይቀር ዘገባው አስታውሷል


የኔነህ ከበደ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page