በደቡብና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ትናንት ምሽት ከሰማይ የወረደው ተቀጣጣይ ነገር ምንነት እያጣራ መሆኑን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ተናገረ፡፡
ምንነቱን ካጣራሁ በኋላ ለህዝብ ይፋ አደርጋለሁ፤ እስካዚያው በትዕግስት ጠብቁኝ ብሏል፡፡
በአርባ ምንጭ እና ቡርጂ አካባቢ ትናንት ምሽት 1 ሰዓት ተኩል አካባቢ ከሰማይ ወደ ምድር የወረደው ተቀጣጣይ ቁስ ነዋሪዎችን እንዳስደነገጠ በተለያዩ ማህበራዊ ሚድያዎች በስፋት ሲዘዋወር አምሽቷል፡፡
ይህን ተከትሎ የስፔስ ሳይንስ በትዊተር ገጹ በወጣው መረጃ በተጠቀሰው ስፍራ በሰማይ ላይ እተቀጣጠሉ በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ምድር ሲምዘገዘጉ የነበሩ የቁሶች ስብስብ መታየቱን አረጋግጧል፡፡
በደረሰኝ ተንቀሳቃሽ ምስልም ቁሱ የጠፈር ፍርስራሾች አልያም የሚቲዩር አለቶች እንደሚመስል መላምቱን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ጠቅሶ የክስተቱን ተፈጥሮ ወይም ምንነት ለማብራራት ግን ሁኔታውን በቅርበት እያጣራለሁ ነው ብሏል፡፡
Comments