top of page

ጥር 2፣2017 - የፋይናንስ ተቋማት ከሚጠበቅባቸው አንፃር ለታላቁ የህዳሴ ግድብ የሚያደርጉት የገንዘብ ድጋፍ በቂ አይደለም ተባለ

የፋይናንስ ተቋማት ከሚጠበቅባቸው አንፃር ለታላቁ የህዳሴ ግድብ የሚያደርጉት የገንዘብ ድጋፍ በቂ አይደለም ተባለ።


ይህ የተባለው ለግድቡ ግንባታ ማጠናቀቂያ የሚሆን የፋይናንስ ተቋማትን ያሳተፈ የ110 ሚሊዮን ብር የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር በተካሄደበት ወቅት ነው።


ለግድቡ ግንባታ እስካሁን ከ20.2 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን #የታላቁ_ህዳሴ_ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት ዋና ስራ አስፈፃሚ አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር) ተናግረዋል።


ባንኮች፣ ኢንሹራንሶችና ማይክሮ ፋይናንሶች በተለያዩ ጊዜ ለግድቡ ያዋጡ ቢሆንም ምንም አይነት ገንዘብ ያላዋጡ አዳዲስ የፋይናንስ ተቋማት እንዳሉ ተጠቁሟል።

በዛሬው ገቢ ማሰባሰቢያ ለአዳዲሶቹ ተቋማት 60 ሚሊዮን ብር ቦንድ እንዲገዙ ጥሪ ቀርቧል።


በተጨማሪም ከዚህ ቀደም ቦንድ ገዝተው የመመለሻ ጊዜው የደረሰ ቦንድ ያላቸው የፋይናንስ ተቋማት ቦንዱን በድጋሚ እንዲያድሱ በማድረግ 50 ሚሊዮን ብር ይሰበሰባል ተብሏል።


ዛሬ በሸራተን ሆቴል እየተካሄደ በሚገኘው የበገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በድምሩ 110 ሚሊዮን ብር እንደሚሰበሰብ ዶ/ር አረጋዊ ተናግረዋል።


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በበኩሉ ለማጠናቀቂያው ግንባታ የድርሻውን እንደሚያዋጣ ተናግሮ የገንዘቡን መጠን በቦርድ ወስኜ እሳውቃለሁ ብሏል።


ሁሉንም አይነት የክፍያ ካርዶች በየትኛው የኤቲኤም ማሽን ላይ የመጠቀም አሰራርን የዘረጋው ኢትስዊች በመርሃ ግብሩ የግድቡ ግንባታ 5 ሚሊዮን ብር በስጦታ አበርክቷል።


ምንታምር ፀጋው

Comments


bottom of page