top of page

ጥር 20 2017 - የማሻሻያ ስራዎችም ሲጠናቀቁ ከዚህ ቀደም የነበረው የሀይል መቆራረጥ ይቀንሳል ተብሎ ተስፋ እንደተጣለበት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናግሯል

ረጅም ዓመት ያገለገሉ የኤልክትሪክ መሰረተ ልማቶችን የመልሶ ግንባታ መከወን፣ የሀይል አቅርቦትን ለማሳደግ የማከፋፈያ ጣቢያዎችን መገንባት እና ሌሎች ስራዎችን የያዘው ፕሮጀክት መጠናቀቂያው ላይ እየደረሰ ነው ተባለ፡፡


በአዲስ አበባ እና በዙሪያ ባሉ ከተሞች የሚሰሩት የማሻሻያ ስራዎችም ሲጠናቀቁ ከዚህ ቀደም የነበረው የሀይል መቆራረጥ ይቀንሳል ተብሎ ተስፋ እንደተጣለበት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናግሯል፡፡


ለሀይል መቆራረጥ እንደምክንያት የሚነሱ ችግሮችን በመለየት ማሻሻያዎችን እየሰራ እንደሚገኝ የተናገረው ተቋሙ ከሁለት እና ከሶስት አመት በፊት የተጀመሩት አራት አይነት ፕሮጀክቶችም የዚሁ አካል ናቸው ተብሏል፡፡


በተቋሙ እየተከወኑ ያሉት እነዚህ ፕሮጀክቶች ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው ወደ ትግበራ ሲገቡ ከዚህ ቀደም የነበረውን የሀይል መቆራረጥ ከግማሽ በላይ ይቀንሰዋል ተብሎ ተስፋ እንደተጣለበት የተነገረ ሲሆን የፕሮጀክቶቹ አፈፃፀም 87.9 በመቶ ደርሷል ተብሏል፡፡


አሁን ላይ የሀይል ፍላጎት በመጨመሩ ምክንያት የሀይል መቆራረጥ ይስተዋላል፤ ቀደም ሲልም በእንጨት ፖሎች የተዘረጉ፣ ያለውን የሀይል ፍላጎት መሸከም የማይችሉ መሰረት ልማቶችን አቅም ማሳደግ ላይ ትኩረት አድርጌ እየሰራሁበት ነው ብሏል የኢትዩጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….


ፋሲካ ሙሉወርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page