top of page

ጥር 20 2017 - ‘’የምግብ ዝርዝሩ(ሜኑ) ላይ የጎደሉትን ለመሙላት ማስተካከያ እያደረግኩ ነው’’ የምገባ ኤጀንሲ

‘’የተማሪዎች ምገባ የተማሪዎችን የትምህርት መቀበል አቅም ጨምሯል፤ መሰረታዊ የምግብ ይዘቶች ግን ይጎድሉታል’’ ጥናት


‘’የምግብ ዝርዝሩ(ሜኑ) ላይ የጎደሉትን ለመሙላት ማስተካከያ እያደረግኩ ነው’’ የምገባ ኤጀንሲ


ከአጥኚዎቹ መካከል ሆኑት የስነ ምግብ ተመራማሪው ዶክተር ይሄአለም ታምሩ(ዶ/ር) ምን አሉ?


በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምግብ ሳይንስና የስርዓተ ምግብ ማዕከል ከ2015 እስከ 2016 ዓ.ም የተከወነው ይህ ጥናት፣ በከተማዋ ካሉ ምገባ ከሚደረግባቸው ትምህርት ቤቶች መካከል በ10ሩ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 280 ተማሪዎችን በናሙናነት በመውሰድ ተደርጓል፡፡


በጥናቱ የተዳሰሰው እየተሰጠ ያለው ምገባ በተማሪዎቹ የትምህርት አቀባበል ላይ ምን ለውጥ አመጣ፣ በትምህርት ክትትላቸው ላይ፣ መጠነ ማቋረጥ ላይ ያመጣው ያመጣው ለውጥ ምንድነው፣ የሚቀርብላቸው ምግብ ለእድገት የሚያስፈልጉ ንጥረ ነገሮችን ያሟላ ነው ወይ፣ ሲዘጋጅስ የምግብ ፅዳቱ ይጠበቃል ወይ? የሚሉት ተካትተውበታል፡፡


የጥናቱ ግኝቶች፤ ተማሪዎቹን ካለመመገብ ወደ መመገብ አሸጋግሯቸዋል፤የትምህርት አቀባላቸው ጨምሯል፤መጠነ ማቋረጥ ቀንሷል፤ የሚቀርበው ምግብ ግን መሰረታዊ የምግብ ንጥረ ነገሮችን ያሟላ እንዳልሆነ ጥናቱ አሳይቷል፡፡

የእንስሳት ውጤቶች የሆኑት ስጋ፣ እንቁላል፣ ወተት.. ሌላውም ይጎድለዋል፤መስተካከል አለበት ብለዋል አጥኚው፡፡


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምገባ ኤጀንሲ ምላሽ፤-የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሽታዬ መሃመድ፤ በዩንቨርሲቲው የተከወነው ጥናት ወደ እኛ አልመጣም፤እንዲያቀርቡልን እንጠይቃለን፤ ትክክል ነው ምገባው የትምህርት አቀባበል ላይና መጠነ ማቋረጥ ላይ ለውጥ እንዳመጣ አረጋግጠናል ብለዋል፡፡


የምግብ ዝርዝር ላይ ማስተካከያዎችን እያደረግን ነው፤ለአብነትም በዚህ ዓመት እንደ እንቁላል ያሉ የምግብ አይነቶችን አካትተናል ብለዋል፡፡


በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የምግብ ሳይንስና የስርዓተ ምግብ ማዕከል የተከወነው የዚህ ጥናት ውጤት በተግባር ለውጥ እንዲያመጣ የጉዳዩ ባለቤት ለሆኑት የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ፣ለተማሪዎች ምገባ ኤጀንሲ ጥናቱን እንደሚያቀርቡት ከተመራማሪው ከዶክተር ይሄአለም ታምሩ ሰምተናል፡፡


ኤጀንሲው በያዝነው ዓመት 8.5 ቢሊዮን ብር በሆነ ወጪ ከ800 ሺህ በላይ ለሆኑ ተማሪዎች ምግብና የመማሪያ ቁሳቁሶችን እያቀረብኩ ነው ብሏል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. https://tinyurl.com/56crze3d


ምንታምር ፀጋው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page