ጥር 21፣2016 - በአዲስ አበባ የመሬት አገልግሎቶች መታገዳቸው ተሰማ
- sheger1021fm
- Jan 30, 2024
- 1 min read
የመሬት አገልግሎቶች መታገዳቸውን የተናገረው የአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ እግዱ እንከ መቼ እንደሚቆይ በግልጽ አልተናገረም፡፡
በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የመዋቅራዊ አደረጃጀት ጥናት ተከናውኖ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ጸድቆ ወደ ተግባር እንዲገባ የተወሰነውን ውሳኔ መሰረት በማድረግ የሠራተኞች የባህሪ እና የቴክኒክ ፈተና ተሰጥቶ ውጤቱ ይፋ መደረጉን ቢሮው አስታውሷል።
በዚህም አዲስ በተጠናው መዋቅራዊ አደረጃጀት ጥናት መሰረት የሰራተኞች ድልድል ተሰርቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ ከዛሬ ጥር 21፣2016 ዓ.ም ጀምሮ የመሬት አገልግሎቶች በጊዜያዊነት ታግዷል ተብሏል።
ቢሮው ይህን እንዲያውቁትም ለሁሉም ክፍለ ከተሞች ደብዳቤ ጽፏል፡፡
ሸገር ከዚህ በፊት በሰራው ዘገባ ፈታና የተቀመጡ የከተማዋ የመንግሰት ሰራተኞች ደልድላቸውን ባለማወቃቸው እንደ መሬት ነክ ባሉ አገልግሎቶች ሰራተኞች በስራ ገበታቸው ላይ አንዳልነበሩ መዘገቡ ይታወሳል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments