top of page

ጥር 21 2017 - ኢሰመኮ ‘’ተፈናቃዮች ለመፈናቀላቸው ምክንያት የሆኑ ችግሮች ሳይፈቱ እየተመለሱ ለዳግም መፈናቀል እየተዳረጉ ነው’’ ሲል ተናገረ

‘’ተፈናቃዮች ለመፈናቀላቸው ምክንያት የሆኑ ችግሮች ሙሉ በሙሉ ሳይፈቱ እየተመለሱ ለዳግም መፈናቀል እየተዳረጉ ነው’’ ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ተናገረ፡፡


ተፈናቃዮች ወደ ቀድሞ ቄያቸው ሲመለሱ ይሁንታቸውን ሊጠየቁ ይገባልም ሲል ኮሚሽኑ ተናግሯል፡፡

በተለይም ተፈናቃዮችን መልሶ ከማቋቋም ጋር ተያይዞ መንግስት ሊተገብራቸው የሚገቡ ነገሮች ቢኖሩም እየተከወኑ አይደለም ሲል ኮሚሽኑ ነግሮናል፡፡


እንደ ምሳሌም በካምፓላው ስምምነት መሰረት ተፈናቃዮቹ በጦርነት ምክንያት ቀያቸውን ለቀው እንደመውጣታቸው መንግስት ከመመለሱ በፊት ሰላሙን ማረጋገጥ ይጠበቅበታል ተብሏል፡፡


ይህ ባለመሆኑ ግን ለዳግም መፈናቀል እየተጋለጡ መሆኑን ኢሰመኮ አሳውቋል፡፡


ተፈናቃዮችን በዘላቂነት ለማቋቋም የሚደረጉ ጥረቶችን ኢሰመኮ ያበረታታል ክፍተቶንም በዚህ ልክ እንዲስተካከሉ ይወተውታል ብሏል፡፡



ማርታ በቀለ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page