ለወራቶች በተጠባባቂ ኮሚሽነር ሲመራ የነበረው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አዲስ ኮሚሽነር ሊሰየምለት ነው፡፡
የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ነገ በሚያካሂደው 17ኛ መደበኛ ስብሰባው ለ #ኢትዮጵያ_ሰብአዊ_መብቶች_ኮሚሽን እጩ ዋና ኮሚሽነር ሹመት ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ኮሚሽኑን ለአምስት ዓመታት የመሩት ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ባለፈው ሰኔ 2016 ዓ.ም ላይ የአገልግሎት ጊዜያቸው በማብቃቱ ሀላፊነታቸውን መልቀቃቸው ይታወቃል፡፡
የዋና ኮሚሽሩን የአገልግሎት ጊዜ ማብቃትን ተከትሎ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር የነበሩት ራኬብ መሰለ በተጠባባቂ ኮሚሽነርነት እየመሩት ቆይተዋል፡፡
ዶ/ር ዳንኤል በቀለ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ሆነው የተሾሙት ሰኔ 25 ቀን 2011 ዓ.ም ነበረ፡፡
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
ቴሌግራም: https://t.me/ShegerFMRadio102_1
ዌብሳይት: https://shorturl.at/yCz7q
Коментарі