top of page

ጥር 22፣ 2015- የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሹልዝ ለዩክሬይን ምንም ዓይነት የጦር ጄት አንሰጥም አሉ

  • sheger1021fm
  • Jan 30, 2023
  • 1 min read


የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሹልዝ ለዩክሬይን ምንም ዓይነት የጦር ጄት አንሰጥም አሉ፡፡


ጀርመን ባለፈው ሳምንት ለዩክሬይን 14 ሊዮፓርድ 2 ታንኮችን ለመስጠት ቃል መግባቷን ኒውስ 18 አስታውሷል፡፡


አሜሪካም ለዩክሬይን 31 አብራምስ ታንኮችን እሰጥሻለሁ ብላታለች፡፡


በዚህ የተበረታቱት የዩክሬይን ሹሞች አሁን ደግሞ ምዕራባዊያኑ ዘመን አፈራሽ የጦር አውሮፕላኖችን እንዲያቀርቡላቸው ለመጠየቅ አላረፈዱም፡፡


የጀርመኑ መራሄ መንግስት ግን የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) በአሁኑ ወቅት ከሩሲያ ጋር በጦርነት ላይ አይደለም ብለዋል፡፡


በዚህም የተነሳ አገራቸው ጀርመን ለዩክሬይን የጦር ጄቶችን በጭራሽ አትሰጥም ማለታቸው ተሰምቷል፡፡


ከሩሲያ ጋር በጦርነት ላይ ያለችው ዩክሬይን የኔቶ አባል አይደለችም፡፡


የኔነህ ከበደ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page