ኢትዮ ቴሌኮም ባለፈው ሙሉ ዓመት ያገኘሁትን ትርፍ በዘንድሮ ግማሽ ዓመት አግኝቻለሁ አለ።
ኩባንያው በዘንድሮ 6 ወር የሥራ አፈፃፀም 8.18 ቢሊየን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን ተናግሯል።
ይህ በውድድር ገበያ የተገኘ ከፍተኛ ሥኬት መሆኑን የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ሲናገሩ ሰምተናል።
ኢትዮ ቴሌኮም በ 6 ወር ውስጥ 33.8 ቢሊየን ብር ገቢ አግኝቷል።
ይህም ከ እቅዱ 96 በመቶ ነው ተብሏል።
የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዛሬ የስድስት ወር የሥራ አፈፃፀሙን ለጋዜጠኞች ነግረዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም በመጀመሪያው የውድድር ምዕራፍ ያገኘሁት ውጤት ከጠበቁት በላይ ነው ብሏል።
ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ ፍሬሕይወት ታምሩ በሌላው ዓለም ነባር የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የውድድር ገበያ ውስጥ ሲገቡ ወይም ሲከፈት የደንበኛ መሸሽና ሌሎች ፈተናዎች ያጋጥማቸዋል ብለዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም ግን ደንበኛ ለማቆየትና ለማፍራት የሄድኩበት መንገድ የሚፈልገውን ውጤት እንዳመጣ አግዞኛል ብሏል።
የኩባንያው የደንበኞች ቁጥር 70 ሚሊየን መድረሱ በሪፖርቱ ተናግሯል።
67.7 ሚሊየኑ የሞባይል ድምፅ ደንበኛ ነው።
31.3 ሚሊየን የሞባይል ኢንተርኔት ና ዳታ ደንበኛ ነው ተብሏል።
ኩባንያው በድርድርና የግዢ ሥርአቱን የቀለጠፈ በማድረግ በ 6 ወር ውስጥ 3.5 ቢሊየን ብር ወጪ መቀነሱን ተናግሯል።
የቴሌ ብር ደንበኛ 27.2 ሚሊየን ደርሷል የተባለ ሲሆን 217 ቢሊየን ብር ተገላብጧል ተብሏል። በ 6 ወር ውስጥ 166 ቢሊየን ብር በቴሌ ብር ተላውሷል ።
ኩባንያው በዘንድሮ ስድስት ወር የውጭ ምንዛሪ እጥረት፣የሀይል አቅርቦትና መቆራረጥ ያጋጠሙኝ ችግሮች ናቸው ብሏል።
ተህቦ ንጉሴ
ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
https://bit.ly/33KMCqz
Comments