የምልክት ቋንቋ በህግ ደረጃ የተደገፈ አንድ ቋንቋ እንደ ሀገር ሊደረግ እንደሚገባ ተነገረ፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ከ5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች መስማት የተሳናቸው ናቸው ተብሎ ይታመናል ተብሏል፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋዎች ጋዜጠኝነትና ኮሚዩኒኬሽን ኮሌጅ ሀላፊ አማኑኤል አለማየሁ (ዶ/ር) #የምልክት_ቋንቋ በታሰበው ልክ እያደገ አይደለም ብለዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ባለፉት 15 ዓመታት ቋንቋውን ለማሳደግ ከመጀመሪያ ዲግሪ ጀምሮ እስከ 2ተኛ ዲግሪ ድረስ ተማሪዎችን እያሰለጠ ይገኛል ተብሏል፡፡
ነገር ግን ኢትዮጵያ ውስጥ መስማት የተሳነው ዜጋ ቁጥር እና የቋንቋው እድገት የሚመጣጠን አይደለም ሲሉ ዶ/ር አማኑኤል ነግረውናል፡፡
ይህን ክፍተት ለመሙላት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አጫጭር ስልጠናዎች እየሰጠ ይገኛል ያሉት ዶ/ር አማኑኤል አለማየሁ ሥልጠናው ማንኛውም ሰው እንዲማር እያደረግን ነው ብለዋል፡፡
አሁንም ቢሆን የምልክት ቋንቋ እንደ አንድ ቋንቋ አድርጎ የመቀበል ነገር ህብረተሰቡ ውስጥ እንደ ክፍተት እየታየ ነው ብለዋል፡፡
ከነገ ጀምሮ አዲስ አበባ ላይ የሚደረገው ዓለማቀፍ የምልክት ቋንቋ አውደ ጥናት እንደ ሀገር ቋንቋውን በህግ ደረጃ የፀደቀ አንዱ ቋንቋ ለማድረግ የሚረዱ ጥናትና ምርምሮች ይገኙበታል ተብሎ ይታመናል ሲሉ ነግረውናል፡፡
15ተኛው ዓለማቀፍ የምልክት ቋንቋ አውደ ጥናት ከነገ ጥር 6 እስከ 9 2017ዓ.ም ድረስ ለ4 ተከታታ ቀናት አዲስ አበባ ውስጥ ይካሄዳል፡፡
በረከት አካሉ
Comments