top of page

ጥር 6፣2017 - ''ድህነትን የሚያባብስና ዜጎችን ለተደራራቢ የወጪ ጫና የሚዳርግ ነው'' በሚል ሲያከራክር የነበረው የንብረት ታክስ አዋጅ ፀደቀ

ድህነትን የሚያባብስና ዜጎችን ለተደራራቢ የወጪ ጫና የሚዳርግ ነው በሚል ሲያከራክር የነበረው የንብረት ታክስ አዋጅ ፀደቀ፡፡


የህንፃዎች የገበያ ዋጋ ተገምቶ የዋጋው 25 በመቶውን መነሻ በማድረግ ታክስ እንዲከፈልበት የሚያስገድደው የንብረት ታክስ አዋጅ የመንግስት ተቋማትን እና በጎ አድራጊ ድርጅቶችን ከታክስ ነፃ አድርጓል፡፡


የሃይማኖት ተቋማትም ለአምልኮ እና ለቀብር አገልግሎት የሚጠቀሙባቸው ህንፃዎች ብቻ #የንብረት _ክስ እንደማይከፈልባቸው ተነግሯል፡፡

በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ አዋጁ ሲፀድቅ እንደሰማነው የዝቅተኛ ገቢ ባለቤት የሆነ የአንድ ቤተሰብ መኖሪያ ቤት ያለው ታክስ አይከፍልም ይላል አዋጁ፡፡


ይሁንና ዝቅተኛ ገቢ ያለው ማን ነው? የሚለው አለመወሰኑ አሻሚ ያደርገዋል ሲሉ የፓርላማ አባላት አንስተዋል፡፡


ከባንክ ብድር ወስዶ መኖሪያ የገነባ #የመንግስት_ሰራተኛ ከደመወዙ 35 በመቶ የገቢ ግብር ተቆርጦበት የሊዝ የጣሪያና የግድግዳ ግብር ከፍሎ፣ የአከራይ ተከራይ ተቆርጦበት፣ በዚያ ላይ የባንክ ወለድና ብድር እየከፈለ የንብረት ታክስ ቢጣልበት መክፈል ይችላል ወይ? ሲሉ እንደራሴዎች ጠይቀዋል፡፡


ብዙ ያከራከረው ይኸው አዋጅ በ4 ተቃውሞ፣ በ10 ድምፀ ተአቅቦ እና በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… https://tinyurl.com/yc4eb9hz


ትዕግስት ዘሪሁን

Comments


bottom of page