በማስሎው (Hierarchy of needs) መኖሪያ ቤት ልክ እንደ ምግብ እና ልብስ ሁሉ በመጀመሪያ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ቢሆንም፤ በኢትዮጵያ ግን የቤት ነገር የከፍተኛው የስኬት፣ የሀብት ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
በዚህ ወቅት እገሌ እኮ ቤት አለው መባል የሀብት መገለጫ፣ የስኬት መለኪያ እስከመሆን ደርሷል፡፡
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር እንደሚለው ደግሞ፤ በኢትዮጵያ አሁን ካሉት #ቤቶች 74 በመቶዎቹ ከደረጃ በታች ወይም ለኑሮ የማይመቹ ናቸው፡፡
ስለዚህ ቢንያስ ያለፉትን ሁለትና ሶስት ዓመታት ጨምሮ በአስር ዓመት ውስጥ 4 ሚሊዮን አራት መቶ ሺህ ቤቶች መገንባት አለባቸው፡፡
እንደ እቅዱና እንደተባለው በ4.4 ሚሊዮን ቤቶች ቢገነቡም የቤት ፍላጎቱን መሸፈን የሚቻለው 80 በመቶውን ነው፡፡
ቤቶቹን ማን እንዲገነባቸው ታሰበ? 80 በመቶ ቤቶቹን እንዲገነባ የታሰበው የግል ዘርፍ ነው፡፡
3.5 ሚሊዮን ቤቶችን የግሉ ዘርፍ እንዲገነባ ይፈልጋል፡፡ በቤት ግንባታ ዘርፍ ዋና ዋና ከሚባሉት ችግሮች መካከል መሬትና ገንዘብ ቀዳሚዎቹ ናቸው፡፡
መሬቱ ከየት ይጣል? ገንዘቡንስ ማን ይሰጣል?
ንጋቱ ሙሉ