በቡርኪናፋሶ ሰሜናዊ ግዛት 50 ያህል ሴቶች በታጣቂዎች ታግተው መወሰዳቸው ተሰማ፡፡
እገታውን የፈፀሙት ፅንፈኞች እንደሆኑ በብርቱ መጠርጠሩን RNZ ሬዲዮ በድረ ገፁ ፅፏል፡፡
ታጣቂዎቹ የ50 ያህል ሴቶች እገታ የፈፀሙት በሰሜናዊቱ አርቢዳንዳ ከተማ ነው ተብሏል፡፡
አገሪቱ የፅንፈኞች የጥቃት ዒላማ ከሆነች ቆይታለች፡፡
ለቡርኪናፋሶ የፅንፈኞቹ ጉዳይ የተቸገረ ነገር የጠፋ ለመላ እየሆነባት ነው፡፡
በዚሁ ተፅዕኖ ምክንያት 2 ሚሊዮን ያህል ሰዎች ለመፈናቀል እንደተገደዱ ይነገራል፡፡
አገሪቱ በቅርቡ ተደራራቢ ወታደራዊ የመንግስት ግልበጣዎች እንደተካሄዱባት ዘገባው አስታውሷል፡፡
የኔነህ ከበደ
ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Comments