top of page

ጥር 8፣2016 - በአዲስ አበባ ያሉ የገበያ ቦታዎችን በአንድ ቦታ የሚያገኙበት መተግበሪያ ይፋ ሆነ

መተግበሪያው ‘ሞል ኢን አዲስ’ እንደሚባል ሰምተናል፡፡


ሜልፋን ቴክ በተሰኘ ሀገር በቀል የቴክኖሎጂ ኩባንያ የተሰራው ሞል ኢን አዲስ መተግበሪያ በወጣት ኢትዮጵያዊያን የተሰራ መሆኑ ተነግሯል።


መተግበሪያው ፈጣን እና የእለት ተዕለት ህይወትን በማቅለል በኩል ዓይነተኛ ሚና ይጫወታል ተብሏል።


ሞል ኢን አዲስ መተግበሪያ ካሉበት ቦታ ሆነዉ በቀላሉ የሚፈልጉትን አግልግሎት ወይንም ምርት፤ ለምሳሌ ሲኒማ ቤት፣ ጸጉር ቤት፣ ባንክ ቤት የመሳሰሉትን ፣ የሚከራዩ ቢሮዎችን፣ የስራ ማስታወቂያዎችን እናም ሌሎች መረጃዎችን የት አካባቢ እና የትኛዉ ሞል ላይ እንደሚያገኝ በካርታ ጭምር የሚያሳይ መሆኑ ተነግሮለታል።


እንዲሁም ባሉበት ቦታም ሆነዉ ማመልከት የሚችሉበት፤ ለገባያ አዳራሽ በለቤቶች የሚከራዩ ቢሮዎችን ያለምንም ደላላ ማስተዋወቅ፣ የስራ ማስታወቂያዎችን መልቀቅ፣ ህንጻቸውን በዘመነ መንገድ ማስተዳደር፣ የተከራዮቻቸዉን ምርታቸዉን እና አገልግሎታቸውን እንዲያስተዋውቁ ያደርጋል ተብሏል።



ሞል ኢን አዲስ ይዞ የመጣው መልፋን ቴክ ኩባንያ በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፍ ከአምስት አመታት በላይ እየሰራ የሚገኝ ተቋም መሆኑን ተናግሯል፡፡


የተለያዩ የሶፍትዌር ስራዎችን፣ የሞባይልና የኮምፒውተር አፕልኬሽኖችን፣ የተቋማትን ሲስተም ማበልፀግን እና ለዲጂታል ኢትዮጵያ እቅድ የበኩሉን አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ይገኛል ተብሏል።


መልፋን ቴክ ከ45 በላይ ለሚሆኑ ባለሙያዎች የስራ ዕድል ፈጥሮ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ድርጅቶች በደንበኝነት አፍርቶ፣ ከ14 በላይ መተግበሪያዎችንም አበልጽጓል ሲብል ሰምተናል።


የድርጅት ሀብት ማቀጃ የኢ-ኮሜርስ መተግበሪያ፣ የንብረት አስተዳደር ስርዓት፣ የትምህርት አስተዳደር ስርዓት፣ የሰው ኃይል አስተዳደር ስርዓት፣ የሆስፒታል አስተዳደር ስርዓት፣ የንብረት አያያዝ ስርዓት፣ በፍላጎት ላይ የተመሰረቱ ሶፍትዌሮችን እና ሌሎችም ስራዎችን ለደንበኞቹ ሰርቶ አስረክቧል ሲሉ የድርጅቱ ባለቤት መልካሙ ምትኩ ተናግረዋል።


ንጋቱ ሙሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



Comments


bottom of page