ከወራት በፊት ከፍተኛ የአገልግሎት ክፍያ ጭማሪ ያደረገው የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በመንፈቅ ጊዜ ከእቅዱ ከ6 ቢሊዮን ብር በላይ ብልጫ ያለው ገቢ ሰበሰበ፡፡
ባለፉት 6 ወራት ተቋሙ 10 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ ነው 16 ቢሊዮን ብር የሰበሰበው፡፡
በተያያዘ ተቋሙ በሰጠው መግለጫ ኢትዮጵያዊ ሳይሆኑ በተጭበረበረ ሰነድ #ፓስፖርት ለማግኘት የሞከሩ ከ13,000 በላይ ሰዎች ላይ እርምጃ ወስጃለሁ ብሏል፡፡
አጭበርባሪ ያላቸውን ሰዎች ትክክለኛ ዜግነት ግን አልገለፀም፡፡
እነዚህ ህጋዊ አሰራሩን ጥሰዋል የተባሉ ሰዎች ሀሰተኛ እና የተጭበረበረ ሰነድ ይዘው መገኘታቸው ተነግሯል፡፡
እንዲሁም በተለያዩ የማጭበርበር ተግባር ላይ ተሰማሩና በህገ ወጥ የደላላነት ስራ ላይ የነበሩ ተጠርጣሪያዎችም በህግ ቁጥጥር መዋላቸውን ሰምተናል፡፡
‘’ደላሎችን ጨምሮ 126 የሚሆኑ በህገ-ወጥ መንገድ የተቋሙን አገልግሎት ለማግኘት የሞከሩት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ወስደናል’’ ሲሉ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5rs
Comments