በአፍሪካዊቱ ደሴታማ አገር ኮሞሮስ ከምሽት እስከ ንጋት የሚዘልቅ የሰዓት እላፊ ሥራ ላይ ዋለ፡፡
የሰዓት እላፊው ሥራ ላይ የዋለው በአገሪቱ በተካሄደው ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ በስልጣን ላይ የሚገኙት አዛሊ አሱማኒ አሸንፈዋል መባሉን ተከትሎ ግጭት በመፈጠሩ እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡
ተቃዋሚዎች አሱማኒ አሸንፈውበታል በተባለው ምርጫ ተጭበርብሯል እያሉ ነው፡፡
በርዕሰ ከተማዋ ሞሮኒ ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ የተቃዋሚዎች ደጋፊዎች ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር መጋጨታቸው ታውቋል፡፡
የሰዓት እላፊውም ይሄንኑ ግጭት የተከተለ ነው ተብሏል፡፡#የሁቲ_ታጣቂዎች
የየመን ሁቲዎች በኤደን ባህረ ሰላጤ አንዲት የአሜሪካ መርከብን በአጥቂ ሰው አልባ በራሪ አካል/ድሮን መምታታቸው ተሰማ፡፡
ሁቲዎቹ ትናንት ምሽት በአሜሪካ መርከብ ላይ የድሮን ጥቃት መሰንዘራቸውን የአሜሪካ የጦር ሹሞች እንደተናገሩ አረብ ኒውስ ፅፏል፡፡
ጥቃት አድርሰዋል የተባሉት ሁቲዎች ግን ፈጥነው ሀላፊዎቹ እኛ ነን አላሉም፡፡
በሌላኛዋ የአሜሪካ መርከብ ላይ ጥቃት የተሰነዘረው አሜሪካ የሁቲዎቹን ንቅናቄ ዳግም በአለም አቀፍ አሸባሪነት መፈረጇን ተከትሎ መሆኑ ታውቋል፡፡
ሁቲዎቹ አሜሪካ ያሻትን ብትለንም እኛ ግን ፍልስጤማውያንን ከመደገፍ ወደ ኋላ አንልም ብለዋል በቃል አቀባያቸው አማካይነት፡፡
ትናንት በሁቲዎቹ የድሮን ጥቃት ተሰንዝሮባታል የተባለችው መርከብ ቃጠሎ አጋጥሟት ነበር ቢባልም የጉዳቷ መጠን በዝርዝር አልተጠቀሰም፡፡
አሜሪካ የየመን ሁቲዎችን ንቅናቄ ዳግም በልዩ አለም አቀፍ አሸባሪነት ፈረጀችው፡፡
ፍረጃው በልዩ ልዩ ማዕቀቦችም ጭምር የታገዘ እንደሆነ የአሜሪካ ድምፅ የእንግሊዘኛው አገልግሎት በድረ ገጹ ፅፏል፡፡
ያም ሆኖ በማእቀቡ እንደ ምግብ መድሐኒት እና የነዳጅ ዘይት ያሉ መሰረታዊ አቅርቦቶች እንደማይስተጓጎሉ የአሜሪካ ሹሞች ተናግረዋል፡፡
ሁቲዎቹ እስራኤል የጋዛ ዘመቻዋን ካላቆመች በቀይ ባህር ከእስራኤል ጋር አንዳች ቁርኝት ያላቸውን መርከቦች እንደሚመቱ ሲዝቱ ቆይተዋል፡፡
በአሜሪካ እና ብሪታንያም ይዞታቸውን መደብደብ ከጀመሩ ወዲህም ሁቲዎቹ ጥቃታቸውን አላቆሙም፡፡
ሁቲዎቹ በአሜሪካ በቀድሞው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአስተዳደር ዘመን መጨረሻ በአሸባሪነት ተፈርጀው በፕሬዘዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ከአሸባሪነትን ተፍቀው እንደነበር ዘገባው አስታውሷል፡፡
በቅርቡ በአገር ክህደት ክስ የተመሰረባቸው የሴራሊዮን የቀድሞ ፕሬዘዳንት ኧርነስት ባይ ኮሮማ ወደ ውጭ አገር እንደሚያመሩ ተሰማ፡፡
ኧርነስት ባይ ኮሮማ ወደ ውጭ አገር የሚያመሩት በጤና እክል ምክንያት በውጭ አገር ህክምና እንዲከታተሉ በአገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፈቃድ በማግኘታቸው እንደሆነ አልጀዚራ ፅፏል፡፡
የቀድሞው ፕሬዘዳንት ቀደም ሲል ከጥቂት ወራት በፊት በአገሪቱ ተሞክሮ ነበር በተባለ የመንግስት ግልበጣ እጃቸውን አስገብተዋል ተብለው በአገር ክህደት ክስ እንደተመሰረሰተባቸው ዘገባው አስታውሷል፡፡
ኧርነስት ባይ ኮሮማ የመንግስት ግልበጣ ተሞክሮ ነበር ከተባለበት ጊዜ አንስቶ በቁም እስር ላይ ናቸው፡፡
የቀድሞው ፕሬዘዳንት ለህክምና ወደ ውጭ አገር እንዲሄዱ ቢፈቀድላቸውም በፍርድ ቤት የተከፈተባቸው ክስ አለመቋረጡ ታውቋል፡፡
የሴራሊዮን መንግስት የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ አከብራለሁ ማለቱ ተሰምቷል፡፡
የየመን ሁቲዎች በኤደን ባህረ ሰላጤ አንዲት የአሜሪካ መርከብን በአጥቂ ሰው አልባ በራሪ አካል/ድሮን መምታታቸው ተሰማ፡፡
ሁቲዎቹ ትናንት ምሽት በአሜሪካ መርከብ ላይ የድሮን ጥቃት መሰንዘራቸውን የአሜሪካ የጦር ሹሞች እንደተናገሩ አረብ ኒውስ ፅፏል፡፡
ጥቃት አድርሰዋል የተባሉት ሁቲዎች ግን ፈጥነው ሀላፊዎቹ እኛ ነን አላሉም፡፡
በሌላኛዋ የአሜሪካ መርከብ ላይ ጥቃት የተሰነዘረው አሜሪካ የሁቲዎቹን ንቅናቄ ዳግም በአለም አቀፍ አሸባሪነት መፈረጇን ተከትሎ መሆኑ ታውቋል፡፡
ሁቲዎቹ አሜሪካ ያሻትን ብትለንም እኛ ግን ፍልስጤማውያንን ከመደገፍ ወደ ኋላ አንልም ብለዋል በቃል አቀባያቸው አማካይነት፡፡
ትናንት በሁቲዎቹ የድሮን ጥቃት ተሰንዝሮባታል የተባለችው መርከብ ቃጠሎ አጋጥሟት ነበር ቢባልም የጉዳቷ መጠን በዝርዝር አልተጠቀሰም፡፡
የኔነህ ከበደ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments