ከቅርብጊዜ ወዲህ በአንዳንድ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማትና ጋዜጠኞች ላይ ከህግ አግባብ ውጪ አስሮ የማቆየትና ለስርጭት የተዘጋጀ የህትመት ውጤትን የማገድ ድርጊቶች እንደተፈፀመባቸው እንደሆነ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ተናገረ ፡፡
በዚህምሳቢያ ተቋማቱ የእለት ተዕለት ስራዎቻቸውን ለመስራት መቸገራቸውን ከደረሱኝ ሪፖርቶች ለመገን ዘብችያለውም ብሎዋል፡፡
በአስቸኳይጊዜ አዋጅ ውስጥም ቢሆን በጋዜጠኞችና በመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ላይ የሚኖር ተጠያቂነት ህጋዊ ስርአትን የተከተለ ሊሆን ይገባል ሲል ምክር ቤት አስረድቷል ፡፡
ምክርቤቱ በሕገ መንግስት መሰረት ‹ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች፤ሃሳቦች፤አመለካከቶችበነፃ መንሸራሸራቸውን ለማረጋገጥ ሲባል ፕሬስ በተቋምነቱ የአሰራር ነፃነትና የተለያዩ አመለካከቶችን ለማስተናገድ ችሎታ እንዲኖረው በሕግ ጥበቃ ይደረግለታል› የሚለውን አንስቶዋል፡፡
ሆኖምከሕገ መንግስቱ ጀምሮ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን ጥበቃ ለማድረግ የወጡ የሕግ ድንጋጌዎች ቢኖሩም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በሀገሪቱ ህግ መሠረት ተመዝግበውና ፍቃድ አውጥተው የሚሰሩ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ጋዜጠኞችና የህትመት ውጤት በፀጥታ ሃይሎች ከህገ አግባብ ውጪ መታገታቸው በእጅጉ አሳስቦኛል ሲል ምክር ቤቱ በመግለጫው ተናግሯል፡፡
እንደአብነትም በኢትዮ ሃበሻ አሳታሚ ድርጅት በየሳምንቱ እየታተመ የሚሰራጨው ጊዮን መፅሄትና ዋና አዘጋጁ ነሃሴ 19 ቀን 2015 በፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለው ከአንድ ሳምንት በሃላ ዋና አዘጋጁ ያለ ክስ ሲለቀቅ መፅሄቱ ከአንድ ወር ከ 15 ቀን በላይ አልተለቀቀም ፣የትርታ ኤፍ ኤም የፕሮግራም ዳይሬክተርም ጳጉሜ 5 ቀን 2015 ከመኖሪያ ቤቱ በጥፀታ ሃይሎች ከተወሰደ በሃላ ከአንድ ወር ከ20 ቀናት በላይ ክስም አልተመሰረተበትም፤ፍርድ ቤትም ሊቀርብ አልቻለም ሲል ምክር ቤቱ ጠቅሷል።
የወንጀልድርጊቶች ከመፈፀማቸው በፊት መከላከል ተፈፅሞ ሲገኝም አፋጣኝ ፍትሐዊ እርምጃዎችን በህግ አግባብ የመውሰድ ህገ መንግስታዊ ግዴታ የተጣለባቸው የፀጥታ አካላት ጋዜጠኞችን አስሮ መረጃ መሰብሰብና አስሮ ለቀናት ክስ አለመመስረት እንዲሁም የህትመት ውጤትን ከስርጭት ማገድ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማቱ ስራቸውን በነጻነት እንዳያከናውኑ የሚያስተጓጉል ተግባር ነውም ብሎዋል፡፡
በአስቸካይጊዜ አዋጅ ውስጥም ቢሆን በጋዜጠኞችና በመገናኛ ብዙሃን ተቀማት ላይ የሚኖር ተጠያቂነት በህጉ አግባብ ብቻ መከናወን ይኖርበታል ብለን እናምናለን ያለሲሆን ይህ አለመሆኑ ግን ሀገሪቱ በአለም አቀፍ ደረጃ ያላት ገፀታ ላይ ጥላ የሚያጠላ ሆኖ አግኝቼዋለሁም ሲል ምክር ቤቱ አሰገንዝቧል፡፡
የፍትህአካሉ የተለያዩ ማሻሻያዎች እየተደረጉበት ያለ ቢሆንም ጋዜጠኞችንና ተቋማቱን በተመለከተ በሕጉ አግባብ ተደጋጋሚ የመብት ጥሰቶችን ለማስቀረት ያለመቻሉ ምክር ቤቱ በእጅጉ እዳሳሰበኝ እወቁልኝ ብሎዋል፡፡
ችግሩእንዲፈታም በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ጉዳዩን በማሳወቅ ክትትል እየተደረገ እንደሚገኝ አክሎዋል ፡፡
በመሆኑምመንግስት የወንጀል ተግባሮችን የመከላከል፣ የመመርመር እና ተጠያቂነትን የማረጋገጥ ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ የፍትሕ ሥርዓቱ በአስቸካይ ጊዜ አዋጅ ድንጋጌ ውስጥም ቢሆን በጋዜጠኞችና በመገናኛ ብዙሃን ተቋማቱ ላይ የሚፈፀሙ የመብት ጥስቶችን በህጉ አግባብ ብቻ እንዲመራ በማድረግ ህገ ወጥ የወንጀል ድርጊቶችን በተቻለ ፍጥነት በማረም ሕገመንግስታዊ ግዴታውን እንዲወጣ እጠይቃለው ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት መናገሩን ሰምተናል፡፡
ማርታ በቀለ
የሸገርንወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Comments