ጥቅምት 15፣2017 - የባህር ማዶ ወሬዎች
- sheger1021fm
- Oct 25, 2024
- 1 min read
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዘዳንት ሲሪል ራማፎሣ የፍልስጤማዊያኑን መሪ ማሐሙድ አባስን ምንግዜም ከጎናችሁ ነን አሏቸው፡፡
ራማፎሣ እና አባስ ከብሪክስ ጉባኤ በተጓዳኝ በካዛን የገፅ ለገፅ ንግግር ማድረጋቸውን TRT አፍሪካ ፅፏል፡፡
ደቡብ አፍሪካ እስራኤል በጋዛ የጦር ዘመቻዋ የዘር ማጥፋት እየፈፀመች ነው በሚል በተባበሩት መንግስታት ችሎት ፊት እንደገተረቻት መረጃው አስታውሷል፡፡
አፍሪካዊቱ አገር ፍልስጤማውያን የነፃ አገር ባለቤቶች መሆን አለባቸው የሚለው እምነቷ የጠነከረ መሆኑ ይነገራል፡፡
ማሐሙድ አባስም ለዚህ ሁሉ ደቡብ አፍሪካን በእጅጉ ማመስገናቸው ተሰምቷል፡፡
ደቡብ አፍሪካ ነባር የብሪክስ አባል ሀገር ነች፡፡

የሱዳን መንግስት ጦር በሴናር ግዛት የምትገኘውን የአል ሰዱኪ ከተማን መልሶ በእጁ አስገባት፡፡
ቀደም ሲል ዲንዴርን ከተማ መያዙን ሱዳን ትሪቢዩን አስታውሷል፡፡
ጦሩ አል ሱኪን የያዛት አል ዲንዴርን በተቆጣጠረ 24 ሰዓታት ባልሞላ ጊዜ ነው ተብሏል፡፡
በተለይም አል ዲንዴር የሴናር እና የገዳሪፍ ግዛቶችን የምታገናኝ ቁልፍ ከተማ እንደሆነች ተጠቅሷል፡፡
በሴናር ግዛት ተፋላሚዎቹ የሚያካሂዱት ውጊያ ከበድ ያለ ነው ተብሏል፡፡
የሱዳን መንግስት ጦር እና በምህፃሩ RSF የተሰኘው ፈጥኖ ደራሽ ሀይል ጦርነት ማካሄድ ከጀመሩ ከአመት ከመንፈቅ በላይ ሆኗቸዋል፡፡
Comments