የቴክኒካል እና የገንዘብ ድጋፍ አለማግኘታቸው ስራ ፈጣሪዎች እንዳይበራከቱ እንቅፋት መሆኑም ተነግሯል፡፡
ስራ ፈጣሪዎች በሚፈለገው ልክ ወደ ፊት አለመውጣታቸው የስራ አጥ ቁጥሩን እንዳይቀንስ አድርጎታል ተብሏል፡፡
ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች የሚያስፈልጋቸውን ቴክኒካል እና የገንዘብ ድጋፍ አለማግኘታቸው ዋነኛው ችግር ነው፡፡
በተጨማሪም ለስራቸው ምቹ ቦታ አለማግኘታቸው፣ የታክስ ሥርዓቱ ለጀማሪ የስራ ፈጠሪዎች የተመቸ አለመሆን እና ሌላ ሌላውም ችግር ወደ ፊት እንዳይወጡ እና በሚፈለገው ልክ ስራ ፈጣሪዎች ወደ ገበያው እንዳይገቡ ያደርጋቸዋል ይላሉ በዘርፉ ላይ የሚሰራው ዊቬንቸር የተሰኘ ድርጅት ስራ አስኪያጅ የሆኑት ማክዳ ፀጋዬ፡፡
ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች በተገቢው መንገድ አለመታገዛቸው እንደ ሀገር ምን አሳጥቶናል ብለን የጠየቅናቸው የዊቬንቸር መስራች ማክዳ ፀጋዬ የስራ አጥ ቁጥሩ እንዲጨምር ምክንያት መሆኑን ይናገራሉ፡፡
በሌሎች የአለም ሀገራት ከ80 በመቶ በላይ የስራ እድል የሚፈጠረው በጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች መሆኑን የሚናገሩት ማክዳ ፀጋዬ ስራ ፈጣሪዎችን አለመደገፋችን የስራ አጥ ቁጥሩ እንዳይቀንስ አድርጎታል ይላሉ፡፡
ዘርፉ አለበት የተባለውን ችግር ለመፍታትም እየሰራሁ ነው ያለው ዊቬንቸር የተሰኘው ድርጅት ስራ ፈጣሪዎችን መደገፍ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ሥነ ምህዳሩ ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ ሲነገር ሰምተናል፡፡
ስራ ፈጣሪዎችን በተለያየ መንገድ ድጋፍ እያደረገ ያለው ዊቬንቸር የተሰኘው ድርጅት በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ የገባው ከአመት በፊት ነው፡፡
ፋሲካ ሙሉወርቅ
コメント