ከወር ገደማ በፊት የፍልስጤማውያኑ የጦር ድርጅት /ሐማስ/ በእስራኤል ላይ ድንገት ደራሽ ጥቃት ሲያደርስ ከ200 በላይ ታጋቾችን ወደ ጋዛ መውሰዱ ሲነገር ሰንብቷል፡፡
ሐማስ ይዟቸው ከሰነበቱ ታጋቾች በሰብአዊ ርህራኔ በሚል ምክንያት የለቀቀው ጥቂቱን ብቻ ነው፡፡
እስራኤል በምድር ሀይል በከፈተችው ጥቃት ታጋቾቹንም የማስለቀቅ አላማም ያለው ነው ተብሏል፡፡
አሜሪካም ይሄን ግዳጅ የሚረዱ የልዩ ሀይል ወታደሮቿን ወደ ጋዛ እንደምትልክ ታይምስ ኦፍ እስራኤል ፅፏል፡፡
ይሁንና ምን ያህል የአሜሪካ ልዩ ሀይል ወታደሮች በዚህ ግዳጅ እንደሚሰለፉ የተጠቀሰ ነገር የለም፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Comments